በኮቪድ ወረራ በመጨረሻ ተጠቂ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል እየታየ ነው 5/8/2020
 


ለዘመናት በብዙ ነገር የተንጋደደ አድልዎ ያለበት የአኗኗር ሁኔታ ለእንደዚህ አይነት ክፉ ጊዜ ለጥቃት አመቺ ሆኖ መገኘትን ይፈጥራል፡፡ ይህ ማህበረሰብ፣ ከትምህርት ደረጃ፣ ከሥራ ደረጃ፣ ከገቢ መጠን፣ ከመኖሪያ ቤትና የአካባቢ አኗኗር ከሌሎቹ የህብረተ ሰብ ክፍሎች ባነሰ ሁኔታ የነበረና ያለ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ በቂ የጤና አንክብካቤ አለማግኘት፣ ብዛት ላላቸው ተደራቢ በሽታዎች በመጋለጥ፣ ለኮቪድ-19 አመቺ የጥቃት ሜዳ መክፈቱ ግልፅ ነው፡፡

ይህ በአሜሪካ ነው አንግዲህ፣ ሰለ የትኛው ህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡

አሁን መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በኮቪድ ምክንያት የአፍሪካን አሜሪካን (ጥቁር አሜሪካውያን) ማህበረሰብ በሰፊው እየተጎዳ ነው፡፡

1ኛ.  ጥቁሮች በብዛት በሚኖሩባቸው ካውንቲዎች፣ በኮቪድ በመያዝ ሶስት ዕጥፍ፣ በኮቪድ ምክንያት መሞት ደግሞ በስድስት ዕጥፍ ነጮች በብዛት ከሚኖሩባቸው ካውንቲዎች በላይ እየታየ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ፣ የሜሪላንድን ካውንቲዎች አሀዝ መመልከት በቂ ነው፡፡ በሜሪላንድ፣ ፕሪንስ ጆርጅና ሞንተጎመሪ ካውንቲ በመሪነት ይገኛሉ፡፡

2ኛ. በየከተማዎች የተዘገቡተን አሃዞች ተመልከቱ

በቺካጎ፤ በኮቪድ ከተያዙት 50%፣ በኮቪድ ከሚሞቱት 70% ጥቁሮች ናቸው፡፡ በቺካጎ ጥቁሮች፣ ከጠቅላላው ህዝብ ቁጥር 30% ናቸው፡፡

በሉዊዚያና፤ በኮቪድ ምክንያት ከሚሞቱት 70 % ጥቁሮች ናቸው፣ ከአጠቃላይ የስቴቱ ህዝብ ቁጥር ግነ ጥቁሮች 32.3 % ብቻ ናቸው፡፡

በሚቺጋን፤ በከቪድ-19 ከተያዙት 33%፣ ከሚሞቱት ደግሞ 40% ጥቁሮች ናቸው፡፡ ከአጠቃላይ የሚቺጋን ህዝብ ቁጥር ጥቁሮች 14% ፐርሰንት ብቻ ናቸው፡፡

በኮቪድ-19 ወረራ ዋና ማዕከል ከሆነው ከኒው ዮርክ ከተማ፤ በኮቪድ ምክንያት ከሞቱት ጥቁሮች 28% ሲሆን፣ ሂስፓኒክ ደግሞ 34% ናቸው፡፡ በከተማው ህዝብ ቁጥር አንፃር ሲታይ፣ ጥቁሮቹ 22%፣ ሂስፓኒኮች ደገሞ 29% ብቻ ናቸው፡፡ በህዝብ ቁጥር ካላቸው መጠን አነስተኛ ሆነው፣ በኮቪድ-19 ምክንያት መሞት ግን ከቁጥራቸው በላይ የሆነ ድርሻ እየወሰዱ ነው፡፡

በጣም አሳዛኝ፡፡ ይህ አይነት ገፅታ በተለይ በጥቁሮች ላይ በኤች አይ ቪ ሥርጭት ላይ የታየ ነው፡፡

አሁን ለመወቃቀስ ሳይሆን፣ ምን ይደረግ ወደ ሚለው ጥያቄ ነው መሄድ ያለብን

የኮሮና-2 ወይም የኮቪድ ሥርጭትን የገታው ነገር ቢኖር፣ በሌሎች አገሮች አንደታየውም

1ኛ፡ መራራቅ፣ ሰው ከሰው ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት መቀነስ

2ኛ፤ በመንግሥት በኩል፣ የተያዙትን ማወቅ፣ ከነሱ ጋር ንክክ አላቸው ወይም ተጋልጠዋል የሚባሉ ሰዎችን ማወቅና ሁሉም ላይ ምርመራ ማድረግ፡፡

3ኛ፤ ማህበረሰቡ፣ በግልፅ አንደታየው አደጋ ላይ ስለሆነ፣ ለዚህ ማህበረሰብ የተለየ አትኩሮት ተሠጥቶት፣ ምርመራ በስፋት እንዲካሄድ ማድረግ

4ኛ፡ በመርምራ የታወቁትን ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ በተለየ ቦታ አግልሎ ማስቀመጥ (ሆቴሎች በሙሉ አፋቸውን ከፍተው ቁጭ ብለዋል)፡፡ ማደሪያ አልባ ለሆኑ ሰዎች አገልግሎት እየዋሉም ነው፤፤

ነገር ግን መንግሥት ይህን እሰከሚያደርግ ድረስ ህብረተሰቡ በራሱ የሚገባውን ጥንቃቄ በማድረግ፣ በሸታው እንዳይሠራጭ በነፍስ ወከፍ መሥራት አለበት፡፡ አብዛኛው የኛ ማህበረሰብም ከሚገባው ድርሻ በላይ እየተጠቃ ይምሰላል፡፡ አሃዝ ሲገኝ ይወጣል፡፡

አስኪ ከሥር ያለውን፣ የኒው ዮርክ ጤና ቢሮ ያወጣውን ሪፖርት ተመልከቱ፡፡ ይህ ጉዳት ሌላ ሠፈር ነው ያለው ብሎ መዘናጋት ተገቢ አይደለም፡፡

አንድ እንደ ቀልድ የሚነገር ተረት ቢጤ ትዝ አለኝ

ሞትና ነገር ወደነከሌ አገር
ብር ብር ወደነከሌ አገርዋቢ ምንጮች፤

Reyes C, Husain N, Gutowski C, St Clair S, Pratt G, Chicago Tribune. Published April 7, 2020. Accessed April 12, 2020.
Deslatte M. Louisiana data: US News World Report. Published April 7, 2020. Accessed April 12, 2020
Thebault  R , Ba Tran  A , Williams  V . The coronavirus is infecting and killing black Americans at an alarmingly high rate. Washington Post. April 7, 2020
New York State Department of Health. COVID-19 fatalities. Updated April 11, 2020. Accessed April 12, 2020.

ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ
አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic