​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

Health and History

የበሽታው ምልክቶች፡

 • አይንና ቆዳ ብጫ መሆን
 • የሆድ ህመም
 • የነጣ ሠገራ
 • ጠቆር ያለ (ደማቅ ሻይ ቀለም) ያለው ሽንት


በአብዛኛው ብዙ ሰዎች ይህንን በሽታ በቀላሉ ይወጡታል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ላይ ግን ከላይ እንደታየው ሕይወት ማለፍም ይኖራል፡፡ ለዚህ በሽታ ድጋፍ የሚሠጥ ሕክምና ውጭ ቀጥታ ቫይረሱን የሚገል መድሐኒት የለም፡፡ በበሽታው አንድ ጊዜ ተለክፈው ያገገሙ ሰዎች በተፈጥሯቸው መከላከያ ሰለሚፈጥሩ መልሰው አይያዙም፡፡
ዋናው ነገር ይህን ቫይረስ በክትባት መከላከል ይቻላል፡፡ መንገደኞች እንደ ኢትዮጵያ ወዳሉ ሀገራት በሚጓዙበት ጊዜ ከሁለት ሳምንታት ቀደም ብለው ክትባቱን እንዲወስዱ ጥብቅ ምክር ይሠጣል፡፡

የአሜሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል(CDC) የሚከተሉት ሰዎች አስቀድመው ክትባቱን እንዲወስዱ መመሪያ አውጥቷል፡፡

 • ሁሉም ዕድሜያቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህፃናት
 • ሔፓታይትስ ኤ በከፍተኛ መጠን የሚተላለፍባቸው ሀገሮች የሚጓዙ መንገደኞች፡፡ ኢትዮጵያንም ይጨምራል
 • ከነዚህ ሀገራት የሚመጡ ሰዎችን የሚንከባከቡ ሰዎች
 • ግብረ መሰል ፆታ የሚያደርጉ ሰዎች
 • ሌላ የጉበት በሽታ ያለባቸው ሰዎች ለምሳሌ እንደ ሔፓታይትሰ ቢ ና ሲ (Hepatitis B and Hepatitis C)
 • የደም መፍሰስ በሽታ ያለባቸው ከሰዎች የሚወሰድ ደም የሚያረጉ ፕሮቲኖችን የሚቀበሉ ሰዎች
 • በሔፓታይትስ ኤ ቫይረስ ምርምር የሚያደርጉ ሰዎች ይጨምራል፡፡

ህም፣ በሀገራችን በተለምዶ የወፍ በሽታ ተብሎ የሚታወቀው፣ የጉበት በሽታ በማስከተል ከሚታወቁ ብዛት ያላቸው ቫይረሶች አንዱ በሆነው በሔፓታይትሰ ኤ ቫይረስ (Hepatitis A) የሚነሳው በሽታ ነው፡፡

በጣም ባይገርማችሁ፣ በሰሜን አሜሪካ ከመጋቢት 2017 ጀምሮ በተለያዩ ከተሞች ይህ በሽታ እየተዛመተ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኔ ራሴ እንኳን ለስብሰባ ወደ ሳን ዲየጎ ጎራ ብየ በነበረበት ጊዜ፣ ስብሰባብውን በጠሩት በባለሙያተኞቹ ማህበር በኩል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶን ነበር፡፡ በአሜሪካ ከተሞች በዚህ በሽታ የሚለከፉ ሰዎች በአብዛኛው መኖሪያ የሌላቸው መንገድ አዳሪዎች(homeless) ፣ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎችና ከነሱ ጋር በቅርበት ንክኪ ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እንግዲህ ይህ በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በመሆኑ ነው አሳሳቢ የሆነው፡፡ በዚህ ሁኔታ በሽታው ሚቺጋን፣ ዩታህ፣ እና ሳን ዲየጎን ጨምር በካሊፎርንያም ተከስቷል፡፡

በተዘገበው መረጃ፣ ይህ ፅሁፍ እስከተፃፈበት ቀን ድረስ፣ ባጠቃላይ 486 ሰዎች ሲለከፉ፣ 413 በሆስፒታል ውስጥ ርዳታ የተደረገላቸው ሲሆን 21 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡ ቀላል ነው ተብሎ ለሚገመት በዚህ በሽታ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሕይወት ማለፍ አሳሳቢ ነው፡፡

በሀገራችን ይህ ቫይረስ በብዛት እንደሚተላለፍ ይታወቃል፡፡ አሳሳቢ የሚሆነው ደግሞ የመተላለፊያ መንገዱ ነው፡፡ ያም ማለት ከምግብ ወደ አፍ ፣ ማለትም የሚመገቡት ምግብና መጠጥ በሽታው ባለባቸው ሰዎች የተዘጋጀ ከሆነ ነው፡፡ ህሙማኑ የነኩትን ምግብና መጠጥ ከተመገቡ በቫይረሱ በቀላሉ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ አዲስ መንገድ ነው ባይባልም እየጨመረ የመጣው ደግም በተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች በሚደረግ ግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካኝነት መተላለፉ ነው፡፡


ዋናው ምክር፣ ወደ ሀገር ቤት በተለይም ልጆችን ይዘው የሚጓዙ መንገደኞች እነሱም ሆነ ልጆቻቸውን ማስከተብ የግድ ነው፡፡

ክትባቱ በስድስት ወራቶች ልዩነት ሁለት ጊዜ ብቻ በመርፌ መልክ ነው የሚሠጠው፡፡ እዚህም ወይም በአውሮፓም እንኳን ቢኖሩ፣ እንደታየው ሁሉ በምግብ አማካኝነት በበሽታው የመለከፍ ዕድሉ ሰለሚኖር ክትባቱን መውሰድ የግድ ነው፡፡ ለምሳሌ በቨርጂኒያ ከቀዘቀዘ strawberry smoothies (እንጆሪ) ጭማቂ 40 ሰዎች የተለከፉ መሆናቸው በነሐሴ በ2016 የመገናኛ አውታሮቹም አራግበውታል፡፡

ድንገት ለበሽታው ተጋልጠው ከሆነ ደግሞ፣ ወደ ህክምና ቦታ ጎራ ማለትና ለዚሁ በሸታው ሳይነሳ ለመከላከል የሚሰጡ ርደታዎችን መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ለመጥቀስ ከተጋለጡ እድሜዎ በ1-40 አመት ውስጥ ከሆነ ክትባት ወዲያውኑ ይሠጣል፡፡ ከዚህ ዕድሜ ክልል ውጭ ለሆኑ ሰዎች ደግሞ ሔፓታይትስ ኤ ቫይሱን ማጥቃት የሚችል የተቀመመ ፕሮቲን (Hepatitis A immunoglobulin) ይሠጣል፡፡ ይህ ፕሮቲን የማይገኝ ከሆነም ክትባት መሥጠት ይቻላል፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን አስቀድሞ መከተብ ጥሩ ይሆናል፡፡ ለራስ ብቻ ሳይሆን ቤተሰብ ውስጥም ሰው ከተለከፈ ወደቀሩት ማስተላለፍ ሰለሚችል መጠንቀቁ ተገቢ ነው፡፡

እንግዲህ ክትባት መውሰድ ከሚገባቸው ወገኖች በኩል ስለሆን፣ ክትባቱን ሀኪሞቻችን እየጠየቅን እንድንወስድ እንመክራለን፡፡ ከአገር ቤት የደረቀ የሌሊት ወፍ ላኩልኝ እንዳንል ምክሩን መቀበሉ ጥሩ ነው፡፡

መልካም ንባብ

ሔፓታይትሰ ኤ (Hepatitis )A