​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

Health and History

የወንዶች ግርዛት ከኤች አይ ቪ(HIV) መከላከል ያስችል ይሆን?

ይህ ጥያቄ ከተነሳ ቆይቷል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች ተካሂደው ማጠቃለያ ሃሳቡ ወይም ውጤቱ በርግጥ በኤች አይ ቪ የመያዝ ሁኔታን ይቀንሳል ነው፡፡ ጥያቄው ደግሞ ታዲያ እንደሱ ከሆን በባህላቸው የወንዶች ግርዛትን ማድረግ አንዱ የሆነ ሀገሮች፤ እንደ ኢትዮጵያ የመሰሉት የበሽታው ሥርጭት ቀንሷል ማለት ነው ወይ? ማለትም ግርዛት ባይኖር ኖሮ አሁን ከሚታወቀው በላይ ሥርጭት ይኖር ነበር ወይ?

ሁሌም ጥናት ሲጠናና ውጤቱ ሲገለፅ እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን ማንሳት አግባብ አለው፡፡ ለማንኛውም ወደ አርስቱ እንመለስና በቅርቡ ሰለተገለፀው ስለ ወንዶች ግርዛት ላካፍላችሁ፡፡ ይህ የተደረገው በኬንያ ነው፡፡ ይህንን የወንዶች ግርዛት በስፋት ለማድረግ ወስነው በታየው ውጤት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ ሳይለከፉ እንደቀሩ ነው ዘገባው የሚያስረዳው፡፡ ለኬንያ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም በሰፊው ለማደረግ የወሰኑት ከዚህ ቀደም በተደረጉ ሶሰት ጥናቶችና ውጤት ተመርኩዘው ነው፡፡ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2008 አስከ 2013 በአስር ሀገሮች ወደ 860 000 የሚሆኑ ወንዶች እንዲገረዙ ታቅዶ በ2013 የተፈለገው ቁጥር ባይደረስም፤ በ2015 ግን 1.2 ሚሊዮን ወንዶች ተገርዘዋል፡፡

ተመራመሪዎች በተለያየ መንገድ በኤች አይ ቪ የሚለከፈውን ሰው ቁጥር ማስላት ችለዋል፡፡ በዚህ ስሌት መሠረት ከ21 000 አስከ 33 000 የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ሳይለከፉ ቀርተዋል፡፡ የተገረዙት ወንዶች በብዛት ወጣቶች ማለትም ከ15 አመት ዕድሜ በታች የሆኑ ሲሆነ በመጠኑም ደግሞ ዕድሜያቸው ከሀያ አራት አመት በላይ የሆኑ ወንዶች አሉበት፡፡ ይህ የመከላከል ችሎታ በዚህ ከቀጠለ፣ በ2030 ከ80 000 እሰከ 160 000 የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ያለመለከፍ ሁኔታ ይኖራል ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ከነዚህ ጥናቶች ውጤት በመመርኮዝ በኬንያ የወንዶች ግርዛት በሰፊው እየተካሄደ ነው፡፡ የወንዶች ግርዛት ከኤች አይ ቪ መከላከያ መንገድ ነው ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ይህ ማለት ግን መግቢያው ላይ እንደጠቀሰኩት የሰዎችን በቫይረሱ የመለከፍ አጋጣሚውን ቢቀንስ እንጂ ጨርሶ ሊያስጥል ስለማይቸል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የተገረዙ ሰዎች በቫይረሱ ተለከፍው ይታያል፡፡