ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ
አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ
Community health
education in Amharic
Copyright 2013. Gosh Health.
All Rights Reserved.
ሁሉም ሰው ሊያውቀው የሚገባ በሰው ዘር ላይ ወንጀል መፈፀም
የተባበሩት መንግሥታት መመዘኛ
Amazing documentaries about Ethiopia Must Watch
Featured
ደረጃ (ትርጉም) | Hgb A1c % | FBS (mg/dl) | OGTT (mg/dl) |
| ጤናማ | Below 5.7 | 99 or below | 139 or below |
ቅድመ ሰኳር በሽታ | 5.7 to 6.4 | 100 - 125 | 140 - 199 |
| የስኳር በሽታ | 6.5 or above | 126 or above | 200 or above |
FBS= Fasting Blood Sugar
OGTT= Oral Glucose tolerance Test
በቅርቡ ስለተጠገነው የአጼ ፋሲል ግንብ ጥያቄ
ማብራሪያ በፕሮጀክቱ ሀላፊ
ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ከሚከተሉት የጤና ቀውሶች አንዱ የኩላሊት በሽታ ነው፡፡ ይህንን የኩላሊት በሽታ ከፋ ደረጃ እንዳይሻገር የሚደረጉ ነገሮች አሉ፡፡ በአብዛኛው፣ አስካሁን ድረስ የሚደረገው፣ ለኩላሊት በሽታ ጠንቅ የሆኑትን የደም ግፊትና የሰኳር በሽታን በመድሀኒት አማካኝነት መቆጣጠር ነው፡፡ ይህ ግን በራሱ፣ እነዚህ በዕደሜ የገፉ ሰዎችን ከሚገባው በላይ ብዛት ያላቸው መድሐኒቶች እንዲወስዱ፣ አንዳንዴም በመድሐኒቶች ምክንያት ጉዳቶች አንዲከሰቱ ነው ያደረገው፡፡ ጥያቄው ታዲያ፣ መድሐኒት ከመስጠት ውጭ ሌላ ምን አይነት ፕሮገራም፣ የኩላሊት በሸታን ወደከፋ ደረጃ ከመድረስ የሚቀነስ ነገር አለ ወይ ነው፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
ዕድሜያቸው ከ45 አመትና ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች ሊያነቡት የሚገባ አዲስ የአንጀት ካንሰር ቅድሚያ ምርመራ (screening) መመሪያ
ለዚህ አዲስ የአንጀት ካንስር ቀድሚያ ምርመራ መለወጥ ምክንያት በ43 አመቱ ሕይወቱ ያለፈው የሲኒማ ተዋናይ ነው፡፡ ብላክ ፓንተር የሚባለውን ሲኒማ ያየ ሰው ኮከብ ተዋናዩን ያስታውሳል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
መሀል ደረትዎ ውስጥ የሚያቃጥል ህመም የሚሰማዎት ከሆነ ይህን ማንበብ ሊረዳዎት ይችላል ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
በወሬ በወሬ እየሰማን ጉዳዩን ብዙም ትኩረት አልሠጠነውም ነበር፡፡ የሚያመክን ክትባት አለ ሲባል፣ የመጀመሪያው ጥያቄ ውነት ነው ወይ የሚለው ነው፡፡ ከጓደኛዬ ጋራ ሀሳብ ስንለዋወጥ፣ ክትባቱ በስህተት ማምከን የሚችል መድሐኒት ጋር ተነካክቶ ይሆናል ወይም እንደዚያ የሚባል ነገር ሰምቻለሁ ነው፡፡ ነገሩ ትንሽ የሚከነክን ስለሆን በወሬ በወሬ ሳይሆን በሳይንሳዊ መንገድ የተሠሩ ጥናቶችን ለእንባቢ የሚያቀርቡ የህክምና ወይም የጤና መፅሔቶችን ማገላበጥ ጀመርኩ፡፡ እና እራሴንም አስከሚገርመኝ ድረስ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ፅሑፍ አገኘሁ፡፡ ለካስ አዳማጭና አንባቢ ጠፍቶ ነው እንጂ ለወሊድ መከላከያ የሚሆነው ክትባት ከተሠራ ስንብቷል፡፡
July 25, 2021
ዕውነት የመንገድ ሥም በከኒንግሃም መሰየም ነበረበት?
በአዲስ አበባ ከተማ ቁጥራቸው በርከት ያሉ በእንግሊዛውያን የተሰየሙ መንገዶችና ትምህርት ቤቶችም አሉ፡፡ ወደኋላ ታሪክ ሲመረመር፣ የጄኔራል ከኒንግሀም ነገር ጥያቄ አስነሳብኝ፡፡
ነገሩ እንግዲህ ሰፋ ያለ፣ ከኢትዮጵያ ህልውና ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ታሪክ አትማሩ፣ አትስሙ፣ ሲሉ የከረሙት ይህንን ያለፈ አደጋ አንዳይታወቅ፣ ለምናልባትም ያንን ያለፈ አደጋ በተራቀቀ መልክ ለማምጣትም ይሆናል፡፡
ከጣልያን አጭር ወረራ በኋላ፣ ጣልያኖች መሸነፍ ሲጀምሩ፣ በተመሳሳይ ቀን፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ ደብረ ማርቆስ በገቡበት ዕለት በእንግሊዙ ጄኔራል በከኒንግሃም የሚመራው ጦር አዲስ አበባ ይገባል፡፡ ልብ በሉ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ወደ መናገሻ ከተማው ወደ አዲስ አበባ ልምጣ ሲሉ፣ ኒውቦልድ ከተባለው እንግሊዛዊ የተሠጠው መልስ፣ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ወደ መቶ ሺ አርበኛ ኢትዮጵያውያን ተዋጊዎች በአዲስ አበባ ሰለሚገኙ በንጉሡ መምጣት ምክንያት በደስታ ጣልያኖችን ይፈጃሉ የሚል ነበር፡፡ ጃንሆይ፣ የዚህ መልስ አልጣማቸውም፡፡ ከጃንሆይ ጋር አብሮ የሚገኘው ጄኔራል ዊንጌትም በነገሩ ደስተኛ አልነበረም፡፡
በዚህ መሀል፣ ከአዲስ አበባ የሚመጣው ዜና አስቀያሚ ነበር፡፡ “ነፃ አውጭ” የተባሉት የነጭ መኮንኖች፣ ኢትዮጵያውያኑን በገዛ አገራቸው በአንዳንድ ሆቴሎችና በአንዳንድ የህዝብ ቦታዎች እንዳይገቡ ዕገዳ አደረጉ፡፡ ይች ነችና አፓርታይድ፡፡ በዚህ ላይ የጂኔራል ከኒንግሃም አስተዳደር ከነፃ አውጭ ይልቅ አንደ ቅኝ ገዥ አይነት ባህሪም እያሳየ ነበር፡፡ ኢትዮጵያኖችም ሥጋታቸው የነበረው፣ እንግሊዞቹ የያዙትን እንደመሥጠት ጠቅለው ለመያዝ አስበዋል የሚል ነበር፡፡ ለሥጋቱ በቂ ምክንያትም ነበር፡፡ የፈረንሳዩ መሪ ደጎል በዚያን ጊዜም አንዲህ ብሎ ነበር፤ “እንዴት ያለ አንግዳ ነገር ነው፤ ኢንግላንድ አሁን ሁሉንም፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማልያና ሱዳንን ልትይዝ ነው የሚል ነበር፡፡”
በዚህ ላይ ማስታወስ የሚገባን፣ ኤርትራና ሶማሊያ በጣልያን እጅ ሰለነበሩ፣ በእንግሊዞች እጅ ያሉ የጠላት(የኢጣልያ) ቦታዎች ናቸው፣ ሰለዚህ ጣልያን ስምምነት እስክትፈርም ድረስ በእንግሊዞች ሥር መተዳደር ነበረበቸው፡፡ የአስተዳደሩ ፎርሙላ የተያዙ የጠላት ቦታዎች አስተዳደር የሚባል ነበር፡፡ Occupied Enemy Territories Administration በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል OETA፡፡ ጣልያኖቹ እየተዳከሙ በመምጣታቸው እንግሊዞቹ የያዟቸውን የጣልያን ቦታዎች እንደ ቅኝ ግዛት በመቁጠር የሚይዟቸውን ቦታ ማስፋት ቀጠሉ፡፡ እንደምታስታውሱት ኢትዮጵያን ዙርያዋን በተለይም በደቡቡ በኩል የነበሩ ቦታዎች በእንግሊዞች ቅኝ ግዛት ሥር ነበሩ፡፡ የነዚህ ቦታዎች አገረ ገዥዎች፣ በጣልያኖች ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን እየወሰዱ መጠቅለል ይፈልጋሉ፡፡ ይህ አስተዳደር (OETA) ጃንሆይን ሳያማክር በኢትዮጵያም ነፃ የወጡ ቦታዎች በሚል የኢትዮጵያን ቦታዎች ማጠቃለል ጀመረ፡፡ እንግሊዞቹ እየመሠረቱት ከነበረው የፖሊስና ህግ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያውያኑ ሊወስዱ የጠበቁትን የጣልያን ንብረቶች በሙሉ ያለ ምንም ልዩነት መውረስ ጀመሩ፡፡ የኢትዮጵያውያኑ ጥርጣሬም እየጠነከረ ሄደ፡፡ ጃንሆይም ቢሆን በዚህ ጉዳይ እንግሊዞችን ዘራፊዎች ሆኑ በሚል አወገዙ፡፡ የኢትዮጵያ ቦታዎችም አሉ ጃንሆይ፣ ግዛታቸው ለጊዜው ተይዞ ቢሆንም በቅኝ ግዛት ሥር አልወደቀም፤ ሰለዚህ በ OETA ሥር ሊወድቅ አይችልምና ሙሉ በሙሉ ወደኔ ይመለስ አሉ፡፡
ነገሩን የሚያከፋው ሌላው የእንግሊዞቹ ድብቅ አላማም ነበር፡፡ ጃንሆይ በደብረ ማርቆስ እንዳሉ፣ በካይሮ የተቀመጠው የእንግሊዙ ባለሥልጣን፣ ሰር ፊሊፕ ሚቸል፣ ጃንሆይን በጎጃም አስቀምጦ እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ፣ ኤርትራን በሚመለከት፣ ከቀሪው ኢትዮጵያ በተለየ በኢጣልያ ቅኝ ሥር ሰለነበረች በ OETA ፎርሙላ መያዝ መፈለግ ብቻ ሳይሆን፣ ኤርትራ ሲባል ትግራይን ጨምሮ ነው በማለት ትግራይንም በመጨመር ቦታዎቹን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አልፈለገም፡፡ በዚህ ጊዜ፣ እንግሊዞቹ “ታላቋ ኤርትራ” የሚባል ሀሳብ ነበራቸው፡፡
በዚህ ላይ ጃንሆይን ያሳሰባቸው፣ የኢትዮጵያ የባላባት መሪዎች ናቸው፡፡ ከነሱም አንዱ የአፄ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ራስ ሰዩም መንገሻ ነበሩ፡፡ በግዞት ከነበሩበት ከኢጣልያ ተመልሰው በጣልያኑ ጁኔራል ናዚ በቦታቸው እንዲያስተዳደሩ ተሹመው ነበር፡፡ አትቸኩሉ፡፡ ከዚያም ከከእንግሊዞቹ ጋር ይገናኛሉ፡፡ በነገራችን ላይ ራስ ሥዩም ተምቤን ላይ በኢጣልያ ያልደረሰባቸው ነገር አልነበረም፡፡ በሠራዊታቸው ላይ ቦምብና የመርዝ ጋዝ ጨምሮ፡፡ ጣልያን ግን ለማባበል እየሞከረ ነበር፡፡ ራስ ስዩም በኃይለ ሥላሴ ላይ ለማኩረፍ በቂ ምክንያት ነበራቸው፡፡ አባታቸው በቁም ሥር እያሉ ነው የሞቱት፡፡ ሰለዚህ ትልቅ ፍራቻ አለ፤ ነገር ግን ራስ ስዩም የመጀመሪያ የሰላምታ ደብዳቤ ለራስ ካሳ ይልካሉ፣ የናፍቆትና የሰላም ምኞት ነበር፡፡ ለኃይለ ሥላሴ አለመላካቸው ፍራቻውን ጨምሮታል፡፡
ጣልያኖች ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲፈልጉ የሚያባብሏቸው መሪዎች ብዙ ነበሩ፡፡ ሁሉም ቢሆን ከጃንሆይ ጋር ቂም ነበራቸው፣ ተበድለናልም ይሉ ነበር፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሰዎች ቁርጥ ቀን ላይ ነው የሚፈተሹት፡፡
ከራስ ስዩም ውጭ፣ የጎጃሙ ራስ ሀይሉ ደግሞ ሌላው ባለጉልበት መሪ ነበሩ፡፡ እሳቸውም ከጃንሆይ ጋር ትልቅ ጠብ ነበራቸው፡፡ በደብረ ማርቆስ የሚገኙት የጃንሆይ ዕጣ በራስ ሀይሉ እጅ ነበር፡፡ የራስ ሀይሉ ጦርና የአርበኞች ቁጥር እየጨመረ ጃንሆይ ከዊንጌት ጋር ይዘውት ከመጡት ጦር በላይ ነበር፡፡ ጃንሆይ እንግሊዞቹን የጠየቁት ራስ ሀይሉ በካርቱም እንዲዘገዩ እንዲደረግ ነበር፡፡ እንግሊዞቹ የሰሙም አልመሰሉም፡፡ ነገር ግን በዚያን ጊዜ፣ ምንም ባላንጣነት ቢኖራቸውም ራስ ሀይሉ ጃንሆይን እንደሚቀበሉ ገለጡ፡፡ ለጃንሆይ ገቡ፡፡
ንጉሡና አብሯቸው የነበረው ጄኔራል ዊንጌት ሁኔታውን በትግሥት ነው የተቀበሉት፡፡ ይልቁንስ እንዴት ወደፊት እንደሚያጠቁ ነበር የሚያስቡት፡፡ በዚያን ጊዘ ከነበሩ የጣልያን ሀይሎች፣ ሁለት እንዳለ ያልተነኩ ነበሩ፡፡ አንደኛው በወሎ በኩል፣ በደሴ፣ ጄኔራል ፍሩቺ የሚባል ሲሆን ሌላው ደግሞ ጎንደር የመሸገው ጄኔራል ናዚ ነበር፡፡ የፈረደበት ጎንደር አንድ አመት ትርፍ ተይዞ የነበረው በዚሁ በጄኔራል ናዚ ምክንያት ነበር፡፡ እነዚህ ሁለት ጄኔራሎቸ ሁኔታውን ይቀለብሱት ይሆን የሚል ሥጋት ነበር፡፡ ሆኖም ጣልያኖቹን፣ አርበኞቹ እነ ፊታውራሪ ብሩ፣ እነ ዳኘው ተሰማ በደፈጣ ውጊያ ከእንግሊዞቹ ጋር በማቀናጀት ጥቃታቸውን ቀጥለው ነበር፡፡ ደብረ ታቦር ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ደብረ ታቦርን ሳይቆጣጠሩ ጎንደር መግባትም የማይሞከር ነው፡፡
ሌላው ሰው ደግሞ የልጅ ኢያሱ ልጅ የሆኑት ልጅ ዮሐንስ ነበሩ፡፡ ህም በኢያሱና በጃንሆይ ያለፈውን ሁኔታ የሚያውቅ ሰው፣ ልጅ ዮሐንስን መጠቀም ይፈልግ ይሆናል፡፡ ጣልያኖችም ሞክረውት ነበር፡፡ ልጅ ዮሐንስ እንደ ራስ ስዩም ሁሉ ለዙፋኑ ተፎካካሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ተፎካካሪ፡፡ ልጅ ዮሐንስ እንደ ብዙ ከጣልያን ጋር አብረው የነበሩ የሚመስሉ በውስጥ ለውስጥ ግን ከአርበኞች ጋር የሚላለኩ ሰዎች አንዱ ነበሩ፡፡ ከራስ አበበ አረጋይ ጋር ይላላኩም ነበር፡፡ ሰለዚህ ጃንሆይ ተመልሰዋል የሚል ዜናና ብዙ ቃል የተገባበት ደብዳቤ ከጃንሆይ ሲደርሳቸው፣ ምንም እንኳን በጃንሆይ ላይ እምነት ባይኖራቸውም ጦራቸውን ይዘው ተቀላቀሉ፡፡ ሰውየውን አይደለም ያዩት፡፡ ኢትዮጵያን ነበር፡፡
በዚህ መሀል ደግሞ፣ ከጃንሆይ ጋር ቁርሾ የነበራቸው ደጃዝማች አያሌው ብሩ ደግሞ በጄኔራል ናዚ ላይ በመነሳት ከእንግሊዘቹ ጦር ከሲመንድስ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በጌምድር አይገነጠልም፣ አለዚያማ እንግሊዞቹ አያሌውን እንዳባበሉ ይታወቃል፡፡ አደጋው ከፍተኛ ነበር፡፡ ጎጃም፣ በጌምድር፣ ወሎ እና ትግራይን ፈልቅቆ ለማውጣትና ንጉሡን ብቻቸውን ለማስቀረት ታስቦ ነበር፡፡ ደባው የገባቸው መሪዎቹ በቁርጥ ቀን ንጉሡን መነጠል ማለት ኢትዮጵያን መሸንሸን መሆኑ ገብቷቸዋል፡፡
ዋናው የተፈራው ትግራይ ትገነጠል ይሆን የሚል ነበር፡፡ ሰለዚህ የራስ ስዩም አካሄድ ወሳኝ ነበር፡፡ በዚህ መሀል ራስ ስዩም ለጃንሆይ በቀጥታ ደብዳቤ ይልካሉ፡፡ በደብዳቤያቸው የገለፁት ዋናው ነገር፣ ሁሉን የሚችለው ፈጣሪ ወደ አገርዎ ሰለመለሰዎ፣ አሁን መደበኛ ነባር ኢትዮጵያን እንዲመሠርቱ ፈጣሪ ይርዳዎት የሚል ነበር፡፡ በራስ ስዩም፣ አገር ወዳድነት፣ ያ ሁሉ ማባበያ እያለ፣ ኢትዮጵያን መረጡ፡፡ ሰለዚህ ጃንሆይ በየቦታው የነበራቸው ሥጋት አገሬን ባሉ ኢትዮጵያውያን መሪዎች ምክንያት ተወገደላቸው፡፡ አሁን ወደ አዲስ አበባ መመለሱን ነው ያተኮሩበት፡፡ በዚህም ምክንያት እንግሊዞቹ የገቡትን ቃል ይፈፅማሉ ለማለት በቂ ምክንያት አላቸው፡፡
ሰለዚህ ወደ አዲስ አበባ እንቅስቃሴው ሲጀመር፣ ደጃዝማች እንዳልካቸው መኮንን በአውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ይልካሉ፡፡ የንጉሡን መመለስ እንዲያዘጋጁ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የጦር መኮንኖችም ወደ አዲስ አበባ እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ ሞጣ ሲደርሱ እንዲመለሱ ታዘዙ፡፡ በአፐሪል 22፣ ሚያዝያ ላይ፣ ከጄኔራል ከኒንግሃም ወደ ዊንጌት ቴሌግራም ይላካል፡፡ ትዛዙም የሚለው ማንኛውንም ንጉሡ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆም ነበር፡፡
ታሪክ ጥሩ ነው፡፡ ዊንሰተን ቸርችል በአፕሪል 9፣ ከከፍተኛ የእንግሊዝ ጦር ባለሥልጣናት (የመከላከያ ኮሚቴ) ጋር ውይይት አድርጎ ነበር እናም ትዛዝ ሲያስተላለፍ ንጉሡ በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ የሚል ነበር፡፡ የዚህ የቸርችል ትዛዝ ሲሰማ ንጉሥ ወደ አዲስ አበባ መንቀሳቀስ ሲጀምሩ፣ ዊንጌት ችግር ላይ ነበር፡፡ ምከንያቱም የጄኔራል ከኒንግሃም ትዛዝ፣ አትንቀሳቀስ የሚለው አልተነሳለትም ነበር፡፡ ሰለዚህ ንጉሡን በጉልበት ማቆም እንደማይፈልግ ይልቁንሰ አጅቧቸው አዲስ አበባ ድረስ እንደሚሄድ ገለፀላቸው፡፡ ንጉሡም በአፕሪል 27 ከደብረ ማርቆስ ተንቀሳቀሱ፡፡ አዲስ አበባም ገቡ፡፡ ንጉሡ አዲስ አበባ ሲገቡ፣ ራስ አበበ አረጋይ መሉ ሀይላቸውን በመያዝ ሁኔታውን ተቆጣጥረውት ነበር፡፡ ከኒንግሃምን የራስህ ጉዳይ እንደማለት ነው፡፡
እንግዲህ ባጭሩም ቢሆን ኢትዮጵያ እንዴት እንደተረፈች ተመልክተናል፡፡ ለውጥ ወይም የሽግግር ሁኔታ ሲፈጠር፣ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ፀረ-ሀገር ሀይሎች የማይሞክሩት ነገር የለም፡፡ በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያን ከመሸራረፍ ያዳኗት፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ባላንጣ የነበሩ፣ ለመበደላቸው በቂ መረጃና ምክንያት የነበራቸው ቀንደኛ የኢትዮጵያ መሪዎች፣ ምንም እንኳን ከጣልያኖች ጋር አብረው የሠሩ ቢመስሉ፣ ቀን ሲያዘነብልና ቁርጥ ቀን ሲመጣ ለአገራቸው በማድላት ይኸው አስረከቡን፡፡ በርግጥ የእንግሊዝ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ቸርችል የሠጡት ውሳኔ ወሳኝም ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ቂም እያላቸው አገሬ ትበልጣለች ብለው ለኢትዮጵያ የወገኑት መሪዎች በተለይም ከላይ የተጠቀሱት አራቱ በየፊናቸው ቢሄዱ ኖሮ፣ ቸርችልና ባላሥልጣናቱ ምን ይወስኑ ነበር ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው፡፡
ቢዘህ ጊዜ፣ እንኳን ለጠላት ለወዳጅም የተባበረ ክንድ ማሳየት በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ባንዳ ሲባል አንሰማለን፡፡ የውነተኛው ከሀዲ ባንዳ በመሪው ላይ ማኩረፉ ሳይሆን በኩርፊያው አሳቦ አገሪቱን ሊበትኑ ካሰቡ ወገኖች ጋር መወገንና ለጥቃቱ መሳሪያ መሆን ነው፡፡ በተለይም አማራጩ እያለው፡፡ የአገር ጉዳይ ሲመጣ የነሱ የግል ቁርሾ ሚዛን አይመታም፡፡ ለበደል በቂ ምክንያት ቢኖርም እንኳን ቅድሚያ ለሀገር መሠጠት አለበት፤ በተለይም አገሪቱ ላይ ትልቅ ጥፋት በሚያንዣብበት ወቅት፡፡ ከራስ ሀይሉ፣ ከልጅ ዮሐንስ፣ ከደጃዝማች አያሌው ብሩ እናም ከራስ ስዩም መንገሻ የምንማረው ይህንኑ ነው፡፡ ከተፎካካሪ በላይ ባላንጣም ነበሩ፡፡ ይሁንና አገር በልጦባቸው አገር አዳኑ፡፡ አሁን፣ በቀጭኑም በወፍራሙ ሰበብ በመፍጠር ከለየላቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር የሚያብሩ፤ ሌሎች ደግሞ ከኩርፊያቸው ብዛት ኢትዮጵያ የራሷ ጉዳይ የሚሉ ወገኖች እየታዩ ነው፡፡ የድሮ ሰዎች ወደው እኮ አይደለም የተቀባ ይንገስ የሚሉት፣ ነጋሽ ነኝ ባዩ በተነሳ ቁጥር ሰላም እንደማይኖር ተገንዘበው ነው፡፡ ወደኋላ ተመልሰን በአዲስ መመዘኛ ባንዳኛቸው ጥሩ ነው፡፡ ያደረጉትን አርገው አገር አስረክበዋል፡፡ አሁን ደግሞ፣ “የተመረጠ ይምራ” ነው፡፡ ህዝቡ በትክክል ተወያይቶበት፣ በነፃና ግልፅ ባለ ሁኔታ መምረጥ ከቻለ፣ ወንበር በዚያ በኩል ነው የሚመጣው፡፡ መምጣትም ያለበት፡፡
እና ስለ ከኒንግሀም መንገድ ምን ትላላችሁ?
ኢትዮጵያውያን፣ አብዛኞቹ፣ ቸርና መሀሪ ናቸው፡፡ ብዙ የታሪክ መረጃዎችም አሉ፡፡ ይቅር ሲሉ ይቅር ነው፡፡ አሁንም በትግሥት እያሳዩት ያለው ባህሪ በማንም አገር ያልታየ ነው፡፡ የተጠበቀው ጎረቤት በጎረቤቱ ይነሳል ነበር፡፡ አልሆነም፡፡ በአጭሩ፣ የኢትዮጵያ አብዛኛው ህዝብ ያልተዘመረለት ጀግና ነው፡፡
እንደኔ እንደኔ፣ የከኒንግሃም ስም ይቀመጥ፣ እንዲያውም ኢትዮጵያ ከከፍተኛ አደጋ ያመለጠችበትን ሁኔታ ማስታወሻ ይሆናል፡፡
ከወደዳችሁት አካፍሉ
ኢትዮጵያ በአውሮፓ ዲፕሎማሲ እንዴት ተረፈች የሚለው መፅሐፍ ብታነቡ ይጠቅማል፡፡ ሰለ ፃፍኩት አይደለም የፃፍኩበት ምክንያት ነው ዋናው ነገር፡፡
ከመቅደላ ተዘርፎ የሄደው አስገራሚው የኢትዮጵያ ቅርስ ያለበት ቦታ ታወቀ፡፡ ሰለ ቅርሱ ከበሬታና ታሪካዊነት የተደረጉ ውይይቶችን ይመልከቱ፡፡
የፈለጋችሁትን በሉ እንጅ ባናለቅስም የተሰማን ጭንቀት ይህ ነው አይባልም፡፡ አዎ ሀኪሞች አንጨነቃለን ግን እንድታውቁብን አንፈልግም፡፡
የሞርጋን ፍሪማን “Finding God” የሚባል ፕሮግራም በናሽናል ጂኦግራፊክ ፕሮግራም እያየሁ እያለ፤ በጨረፍታ ከ9/11 ተረፍኩ የሚል ሰው አየሁኝ፡፡ በአውሮፕላኑ ከጋዩት ህንፃዎች አንደኛው ላይ የነበረ ሰው ነው፡፡ መደምደሚያው እግዚአብሔር አለ ነው፡፡ ድንገት ጋምቤላ ያጋጠመኝ አንድ ሁኔታ ብልጭ አለብኝ፡፡ ልፃፋው አልፃው እያልኩ አመናታሁና ግን ይኸው፡፡
አዬ ልጄ ልጄ እንጀራ ብሎ ተሻገረና
ያለ ዕድሜው ተሹሞ
ቀይ ባሕር ገባልኝ ፈርኦን ሆነና
አይ ጊዜ አይ ንቀት
ተንበርክኮ ያገባትን ተኝቶ ፈታት
አዚህ ነጮች አገር ቀንና ሌሊቱ አልለይ ብሎኝ
ለናንተ በርቶ ይሆን ለኔስ ጨለመብኝ
አስገራሚ መታየት የሚገባው የሩዋንዳ ምስክርነት