​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

Health and History

የበሽታ ስሜት የሌለባቸው ግን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ምን ያህል ይሆን?

 ተዘናግተንም ይሆን፣ ወይም ይህን ያህል አስቸጋሪ በሸታ ጉዳይ ከባለሙያተኞች ውጭ ሲነገር ስለከረመ ይሆን፣ ወይም ደግሞ የዚህን በሽታ አደጋና ክፋት በትክክል መንገር የሚያሰከትለውን ውጤት የጠሉ ወይም የፈሩ ሰዎች የሚያወዛውዙት ጉዳይ ይሆን፣ ብቻ አደገኛነቱ በግልፅ አልተነገረም፡፡ አንዱ ምክንያት የሚሆነው፣ ችግሩ በተነገረ ቁጥር፣ መፍትሄውም አብሮ መቅረብ ሰለሚኖርበት፣ ለመፍትሔው በቂ ዝግጅት ያልተደረገ ከሆነ፣ ችግሩ የለም ወደሚባል ደረጃ የሚደርስ ሁኔታውን ዝቅ ዝቅ ማድረግ የታየበት እንደዚህ በሽታ ታይቶ አይታወቅም፡፡ አንዳንዶቹ ከአቅም ማነሰ፣ ሌሎች ደግሞ ከዝግጅት ጉድለት በሽታው እንዲገን አደርገውታል፡፡

በዚህ መሀል፣ አስፈሪ የሆነው ገፅታ የሚመጣው፣ በቫይረሱ ተይዘው ስሜት የሌላቸው፣ ነገር ግን ቫይረሱን የሚያሰተላልፉ (ሰሜት አልባ) ሰዎች ብዛት ሲገመት ነው፡፡ አንደተገመተውም፣ ለቫይረሱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ መሠራጨት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡ ጤንኘነት ሰለሚሰማቸው፣ ወጣ ወጣ ሰለሚሉም በቫይረሱ በቀላሉ ተጋልጠው፣ እንደ ስንቅ ሰንቀው፣ ሳያውቁት ወደ ቤተሰብ ይዘውት ይሄዳሉ፡፡

በአሜሪካ ከፍተኛ ሥርጭት የሚታይባቸው ቦታዎች

1ኛ. ሰዎች ሰብሰብ ብለው የሚኖሩባቸው ቦታዎች
2ኛ. በቤተሰብ መሀከል፣ ይህ በደንብ የተረጋገጠው በቻይናው ሥርጭት ነው
3ኛ. በጤና ባለሙያተኞች መሀከል ነው፡፡ 
 
ወደ ስሜት አልባ ሰዎች ቁጠር ወይም መጠን ልመልሳችሁና፣ ከተለያዩ ሪፖርቶችና ጥናቶች የተዘገቡትን ውጤቶች ላካፍላችሁ፡፡ መረጃ በመረጃ የተደገፈ ይሁን፡፡ 

ከዚህ በላይ መረጃ የለም ማለትም ይቻላል፡፡ ታዲያ፣ ይህንን ያየ ሰው፣ ሰው ከሰው ጋር መገናኘቱን ይቀንስ ቢል ልክ አይደለም ወይ? እነዚህን ሰዎች ለይቶ ለማወቅና ቫይረሱ፣ በአብዛኛው ጥሏቸው እስከሚሄድ ገለል ለማድረግ፣ የምርመራ ያለህ ቢባል ጩኸቱ የማይሰማው ለምንድን ነው? ይህን እያየንስ፣ ምክር የማይሰሙትን ሰዎች ዝም ብሎ ማየት ይቻላል ወይ፡፡ ሁሉም ሰው መካሪና አስተማሪ ወይም ተቆጬ ለምን አይሆንም?

አሁንም አልረፈደም፣ በውጭ ያላችሁ፣ በስልክ እይደወላችሁ ምክር ስጡ ባካችሁ፡፡ በህዝቡ አጅ ያለ፣ ህብረተሰቡ ማድረግ የሚችለው፣ እነዲያውም ሥርጭቱን ሊቀነስ የሚችለው የሰዎች እንቅስቃሴ ሲገደብ ነው፡፡ ዝም ብሎ የሚታለፍ ነገር አይደለም፡፡

መልካም ንባብ