​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

Health and History

To all who use N95 mask

please see the advice regarding decontamination and reuse

ፊት ላይ የሚደረገውን ማስክ ማጠብና መልሶ መጠቀም ይቻላል ወይ? አዲስ ማሳሳቢያ (4/19/2020)

በተከሰተው እጥረት ምክንያት፣ ፊት ላይ የሚደረጉ ማስኮችን መልሶ መጠቀም እንደገናም መልሶ ማፅዳት ላይ ብዙ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ይህ ባጠቃላይ በደህናው ጊዜ የሚታሰብም አይደለም፡፡ በተለይም N95 የሚባል ማስክ ላይ፡፡ ማስኩ ሲሠራ፣ የተሠራበት ቁስ፣ በውስጡ እንዳያልፉ የሚከልካለቸው ፓረቲክል (ባክቴሪያም ሆነ ቫይረስ መጠን) ተጠንቶ ነው፡፡ ይህ ማስክ በጤና ተቋሞች ወስጥ ለጤና ባለሙያተኞች አግልግሎት የሚውል ሲሆን፣ ሌሎችም ሰዎች በተላላፊው በሽታ የታመሙ ህሙማንን የሚንከባከቡ የቤተሰብ አባላት፣ ወድ ህክምና ቦታ የሚወስድ የድንገተኛ አደጋና አምቡላንስ ሠራተኞች፣ እንዲሁም ከበሽተኞቹ ጋር ቅርበት ወይም ግንኙነት የሚኖራቸው ሰዎች ይገለገሉበታል፡፡

በተፈጠረው ዕጥረት፣ ጥናት በማድረግ የትኛው ማፅጃ መንገድ ቫይረሱን ያፀዳል ወይም በሚገባ ቁጥሩን ይቀንሳል በማለት የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመው ውጤቱን አካፍለዋል፡፡ በተጨማሪም ማሰኩን ለማፅዳት የማይበጁ ወይም ማድረግ የማይገባንን መንገዶች ገልፀዋል፡፡

አስከ አሁን ድረስ፣ እነሱ ይሠራሉ ያሏቸውን መንገዶች፣ የአሜሪካው የበሸታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል፣ አሜን ብሎ ምርቃቱን አልሠጠም፣ ነገር ግን ተቃውሞም አላሰማም፡፡

ሰለዚህ ግለሰቦች፣ የተሠጠውን ምክር በጥንቃቄ እንዲያስተውሉ እመክራለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ፣ በኔ በኩል፣ ይሠራሉ ከተባሉት መንገዶች ውጭ፣ አይሠሩምና አታድርጓቸው የሚለውን ምክር ቅድሜያ እሠጣለሁ፡፡ በሀገር ቤት፣ ይህንን ችግር ለመወጣት ብዙ የማይሆኑ ነገሮች እንደሚደረጉም ሰለሰማን ነው፡፡

ሁለት ጉዳዮች ቢኖሩ፡፡ አንደኛው በማሰኩ ላይ ያለውን ቫይረስ መግደልና ማፅዳት ሲሆን

ሀሉተኛው ጉዳይ ደግሞ፣ መላልሶ ቢጠቀሙ ወይም ባልሆነ መንገድ ቢያፀዱ፣ ማሰኩ ማሾለክ የሚከለክልበት፣ በጥንቃቄ ደረጃ ጠብቆ የተሠራውን የማስኩን ድር ሰለሚያበላሸው፣ መካለከሉ ሊቆምና መከልከል የሚገባቸውን ነገሮች ያሳልፋል፡፡ ያ እንግዲህ የተሠራበትን አላማ ይሥታል፡፡ ተጠቃሚውም ለአደጋ ይጋለጣል፡፡


መልካም ንባብ፣ አካፍሉ ባካችሁ