ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ
አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ
Community health
education in Amharic
ሔፓታይትስ (የጉበት በሽታ)
የጉበት በሽታ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ሲሆን በዚህ ድረ ገጽ ለጊዜው ማተኮር የምንፈልጋው ግን በተላላፊ ቫይረሶች አማከኝነት ሰለሚከተለው የጉበት በሽታ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን በጉበት ላይ ጉዳት በሚፈጠርበት ጊዜ የመጨረሻ ውጤቱ በአብዛኛው አንድ መሆኑ ግልፅ ነው፡
የጉበት በሽታ ከሚያስትሉ ነገሮች ማለትም ከተላለፊ ቫይረሶች ውጭ
አልኮሆል
ወደ ቫይረሶች ስንመለስ ስር የመስደድ ወይም (chronic disease) በማስከተል የሚታወቁት ሔፓታይትሰ ቢ እና ሲ ሲሆኑ ከነዚህ በተጨማሪ ግን አጣዳፊ በሽታ የሚያሰከትሉ እንደ ሔፓታይትሰ ኤ፣ ኤፍና ጂን ይጨምራል፡፡ ሔፓታይትስ ዲ የሚባለው ቫይረስ በብዛት ሔፓታይትስ ቢን ተጠግቶ በመልከፍ ይታወቃል፡፡ ስለ ቫይረሶቹ ጠለቅ ብሎ ለማንበብ ድረ ገፆችን ይጎብኙ፡፡ ወደፊት ተጨማሪና አዳዲስ ፅሁፎች ስለምንጨምር መከታተሉ ይረዳል፡፡