​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

Health and History

Copyright 2013. Gosh Health. 

All Rights Reserved.

​​ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታን በሚመለከት የአቋም መግለጫ

ሕዳር 13፣ 2013 (ኖቬምበር 22፣2020)
 

በጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም (ኖቬምበር 3፣ 2020)፣ በኢትዮጵያ በትግራይ በሚገኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰሜን ዕዝ መከላከያ ላይ የደረሰውን ጥቃትና ተያይዞም በዕዙ አባላት ላይ የተፈፀመውን ኢሰብአዊ የሆነ የግድያና ክብር የጎደለው ሟቾችን የማዋረድ ተግባር ሰንረዳ እንደማንም ኢትዮጵያዊ ሀዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭት የተመለከትነው ነገር ነው፡፡ የተፈፀመውን ድርጊት አሳኝዝነቱን የሚያጎላውም፣ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላት፣ በውስጡ አብረውት ለአመታት ከጎኑ በነበሩ ሰዎች ተባባሪነት መሆኑ ነው፡፡

አንደሚታወቀው፣ ይህ የመከላከያው ሠራዊት፣ ለአመታት ከትግራይ ሕዝብ ጋር በውስጡ አብሮ በመኖር ከጥቃት ሲጠብቀው የነበረ፤ በተጨማሪም በልማት መስክ በሰብል አጨዳና ስብሰባ፣ ተቋማትን በመገንባት፣ በቅርቡ ደግሞ የአንበጣ መንጋጋ ወረራን ከሕዝቡ ጋር በመሆን ሲከላከል የኖረ ኃይል ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ከሕዝቡ ጋር ተሣስሮ እየጠበቀውና በልማት መስክም እየረዳው የሚኖረው ሠራዊት ምንም አይነት የማጥቃት ወይም የዘመቻ እንቅስቃሴ ባላደረገበት በድንገት በማን አለብኘነትና በጠብ አጫሪነት፣ ራሱን የትግራይ ህዘብ ነፃነት ግንባር፣ ባጭሩ ወያኔ፣ ብሎ የሚጠራው ኃይል በሠራዊቱ ወስጥና ከውጭም ባደራጃቸው ኃይሎች ጥቃት በማድረስ የሀገሪቱ ንብረት የሆኑ መሣሪያዎችን መዝረፉም ይታወቃል፡፡ ወያኔ ይህንን ጥቃት አላደረስኩም ብሎ ለማስተባበል ቢሞክርም፣ ለዘመናት የወያኔ የፕሮፖጋንዳና የመገናኛ ሀላፊ የሆነው ሴኩ ቱሬ ጌታቸው የሚባለው ግለሠብ በወያኔ ሜድያ ቀርቦ ወያኔ ጥቃቱን ማድረሱን በገሀድ ያመነበት በምስልና በድምፅ የተደገፈ መረጃ ያሳያል፡፡ እንደ ሴኩ ቱሬ ገለፃ ጥቃቱ፣ በአንግሊዝኛ (Anticpatory Self Defense) አስቀድሞ ማጥቃት የሚባል በመርህ ደረጃ የተወሰደ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህም፣ ወያኔ በጠብ አጫሪነት የፈፀመው ድርጊት ለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡

በቅርቡ በወያኔ የተፈፀሙት ግፍ የተሞላባቸው ወንጀሎች ከዚህ ቀደም ያካሂዱት የነበረው በዘር ወይም በጎሳ አለያይቶ ህዝቡ አርስ በርስ በጥላቻ አይን እንዲተያይና የሰው ሕይወትና ንብረት እንዲጠፋ ያስደረጉበት እኩይ አጀንዳ ቅጥያ ነው ብለን እናምናለን፡፡ የአሜሪካው የሆም ላንድ ሴኩሪቲ በጁን 15፣ 2014 ባወጣው ኦፊሻል ማስታወሻ መሠረት ወያኔ ወይም የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር በደረጃ ሶስት የሚመደብ አሸባሪ ድርጅት ነው ተብሎ መመደቡ ይታወቃል[1]፡፡

ይህንን በማን አለብኘነት በሠራዊቱ ላይ በተፈፀመው ድርጊት፣ የኮቪድ አማካሪዎች ምክር ቤት ያለውን አቋም እንደሚከተለው ይገልፃል፡፡

  1. ወያኔ በሠራዊቱ ላይ ያደረሰው ጥቃት ህግን በመፃረርና በመጣስ የተፈፀመ ኢስብአዊ ድርጊት በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግን የማሰከበር ርምጃ የመውሰድ ሃላፊነትና መብትም አለው፡፡
  2. የወያኔ ሀላፊዎች የፈፀሙት የወንጀል ተግባር የትግራይ ህዝብ ምኞትና ፍላጎት አይደለም፤ ሕዝቡንም አይወክልም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚወስደው አርምጃ ወንጀለኞቹ ላይ ያተኮረ እንጅ የትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም፡፡ ትግራይና የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ሰለዚህ፣ መንግሥት የጀመረውን እንቅስቃሴ በመቀጠል፣ በጥቅምት 24 (ኖቬምበር 3) በሠራዊቱ ላይ ላደረሱት ጥቃት፣ በማይ ካድራ ንፁሀን ዜጎች ላይ ለፈፀሙት ዘር ተኮር ግድያና ላወደሙት የሕዝብ የግንባታ መዋቅሮች፣ የወያኔ አመራሮችን ለፍርድ በማቅረብ ተጠያቂ ማድረግ አለበት ብለን እናምናለን፡፡
  3. ግጭቱ እንዲሰፋ በማቀድ በቅርቡ በባህር ዳር፣ በጎንደርና በኤሪትራ አሥመራ በሲቪል መዋቅሮች ላይ ሮኬት በመተኮስ፣ አያይዞም በሀሰት፣ ግጭቱ ሰፋ ያለ የአፍሪካን ቀንድን ያካተተ ነው በማለት የሚያሠራጩት ፕሮፖጋንዳ አጥብቆ መወገዝና ድርጊታቸውም ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ መጋለጥ አለበት፡፡
  4. የወያኔ ኃይል፣ ለአርባ አመታት ሲንቀሳቀስ፣ ከዚያም አልፎ የሀገሪቱን ሥልጣን በመያዝ በሙሉ ቁጥጥር በሚገዛበት ወቅት፣ በመርህ ደረጃ፣ ዕኩይ በሆነ የሸር ሥራና በህይል ህብረተሰቡን በዘርና በጎሳ በመለያየት የርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠርና እንዲስፋፋ ማድረጉ ተያይዞም፣ የጀምላ ግድያ፣ የግለሰቦች ሞት፣ እንግልት፣ ቤትና ንብረት መውደም፣ ከኖሩበት ቦታ መፈናቀል ዘር ሳይለይ ኦሮሞ፣ አማራና ባጠቃላይ በሁሉም ማህበረሰቦች ላይ  የደረሰ አደጋ ነው፡፡ ነገር ግን፣ የአማራው ሕዝብ ላይ የተለየ አትኩሮት በመሥጠት የመርህ መግለጫ(ማኒፌስቶ) በማዘጋጀት፣ ከተጠቀሱት ጥቃቶች በተጨማሪ ሲኖርበት የነበረውን መሬት በጉልበት መንጠቁ ይታወቃል፡፡ ይህ ኃይል በአሸባሪነት የተፈረጀም ሰለሆነ፣ ባጠቃላይ ህግ ወጥ ቡድን ተብሎ መሰየም አለበት ብለን እናምናለን፡፡ በግፍ ከሕዝብ የነጠቀውን መሬትና ንብረት ለቀዳሚ ሕጋዊ ባለቤቶች መመለስ አለበት ብለን እናምናለን፡፡ 
  5. በወያኔ ኃይሎች በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ምክንያት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት የሚያሳዝነን ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ወቅቱ የኮቪድ-19 አለም አቀፍ ወረርሸኝ በመላው የአለም ክፍል እያደረሰ ያለው አደጋ በኢትዮጵያም ጭንቀትና ጉዳት የፈጠረበት ጊዜ በመሆኑ ችግሩን እንደሚያባብሰው ግልፅ ነው፡፡ በዚህም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ዜጎች በዚህ ግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብ፣ የማህበራዊና የሙያ ርዳታቸውን እንዲለግሡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችም ይህንን ወረርሽኝ ታሳቢ በማድረግ አስፈላጊ ጥንቃቄዎች እንዲደረጉ እንመክራለን፡፡
  6. የአገሪቱ ዜጎች በዘር ተለያይተው ርስ በርስ በጠላትነት እንዲተያዩና ለወያኔ ህገወጥ እንቅስቃሴና ዘረፋ አመቺ ሁኔታ እንዲቀጥል  አይነተኛው ሥር የያዘው ምክንያት፣ ወያኔ በሕገ መንግሥት ደረጃ በህዝቡ ላይ በጭነት ያሠፈረው አገሪቱን በዘር ከፋፍሎ መከለሉ ነው፡፡ የሀገሪቱን ዜጎች በዘርና በጎሣ ሳይለያይ፣ ዘርን መሠረት ያደረገውን አከላልን በማስወገድ፣ ይልቁን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባላቸው መርሆ መሠረት የግለሰቦች መብት፣ ነፃነት፣ ፍትህ ማግኝት፣ በሀገሪቱ በየትኛውም ክፍል በነፃነት ሠርተው የሚኖሩበት ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ  ለወደፊት ዘላቂ ሰላም ያመጣል ብለን እናምናለን፡፡ ሰለዚህ ይህንን ዘርን የተመረኮዘ አከላል ወይም አደረጃጀት መሠረት የሆነው የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በአስቸኳይ ለህዝቡ ለውይይትም ቀርቦ፣ በአገሪቱ ምክር ቤት በህጋዊ መንገድ የሚወገድበት ሁኔታ እንዲፈጠር ጥሪ እናቀርባለን፡፡
  7. በመጨረሻም፣ ማናቸውም የሀገሪቱ ዜጋ፣ ሲፈፀም የነበረውን፣ የተፈፀመውን ግፍና አሰቃቂ ድርጊት አስቀድሞ ነጥሎ በህሊና በመፈረጅ፣ ከወገንተኛነት በነፃ መንገድ፣ ለጠቅላላው ሕዝብ ደህንነትና ለሀገሪቱ ህልውናና ዕድገት ቅድሚያ በመሥጠት፣ ይህንን ድርጊት የሚያራምዱና የሚፈፅሙ ሃይሎችን በጋራ እንዲያወግዝ እንጠይቃለን፡፡


 
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኮቪድ-19 አማካሪዎች ምክር ቤት፣ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ የህዝብ የጤና ቀውሶችን በሚመለከት ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለጤና ባለሙያተኞቸና ለአጠቃላይ ሕዝቡ በሳይንሳዊ መረጃዎች የተደገፉ ምክርና መመሪያዎች ማቅረብን ተልዕኮው ያደረገ የባለሙያተኞች መድረክ ነው፡፡


[1] Department of Homeland Security Policy Memorandum PM-602-0101: Implementation of New Discretionary Exemption Under INA Section 212(d)(3)(B)(i) For Activities and Associations Relating to the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), June 15, 2014.


 

Ethiopian Diaspora High-Level Advisory Council on The Coronavirus List of Members Members of the Council:


Dr. Tilahun Adera, PhD
Professor and Chair
Division of Epidemiology
Senior Associate Dean for Public Health
Virginia Commonwealth University
Former Provost and Vice President
Evangel University


Professor, Demissie Alemayehu
Statistics Department
Columbia University


Samuel Alemu, Esq
Attorney, ILBSG, LLP


Dr. Kebede Begna
Consultant, Division of Hematology
Department of Internal Medicine
Associate Professor of Medicine Mayo Clinic
Vice President, People to People Inc.


Betelhem G Mekonnen
Critical Care Registered Nurse
RN, BSN, RN-BC, PCCN Commissioner
Washington, DC Regional Planning
Commission on Health and HIV (COHAH)


Dr. Kassa Darge,
Professor of Radiology and Surgery
Perelman School of Medicine
University of Pennsylvania,
Radiologist-in-Chief and
The William L. Van Alen Endowed Chair
Department of Radiology
Children’s Hospital of Philadelphia


Dr. Hanna Bewketu Demeke, RN, PhD.
Nurse Consultant
Division of HIV/AIDS Prevention,
Centers for Disease Prevention and Control (CDC)


Dr. Yonas Geda
Professor of Psychiatry and Neurology
Director, Global Health
Barrow Neurological Institute


Dr. Anteneh Habte
Medical Director of the Community Living Center
Veterans Affairs Medical Center
Chairman, People to People (P2P) Board of Directors


Dr. Zelalem Hailu
Virologist,
Associate Director of IDMEL
The Ohio state University,


Dr. Solomon W. Harrar
Professor of Statistics
The Dr. Bing Zhang Department of Statistics
University of Kentucky


Dr. Enawgaw Mehari
Medical Director, Stroke Program
Horizon Hospital, HCA
Adjunct clinical professor of neurology
University of Pikeville
Founder and President People to People Inc.


Dr. Ahmed Moen
Ahmed A. Moen, DrPH, MPH, MHA
Associate Professor and Emeritus Chairman
Department of Allied Health Sciences and Health Management Sciences
College of Nursing and Allied Health Sciences
Department of Family Medicine and Community Health
College of Medicine, Howard University
Associate Senior Faculty
Department of International Health
Johns Hopkins Bloomberg School of Public Health
Baltimore, MD


Dr. Aberra Molla
Veterinarian
CEO of ECS


Dr. Muluken Melese
Senior Technical Advisor for TB and HIV
Management Science for Health


Dr. Girma Tefera
Professor
Interim Division Chair
Division of Vascular Surgery and
Vice Chair of Global Surgery
University of Wisconsin


Dr. Gebeyehu Teferi
Chief of Infectious Diseases
Unity Health Care
Washington D.C.
Founder of GoshHealth.org


Dr. Zelalem Temesgen
Professor of Medicine
Director, Mayo Clinic Center for Tuberculosis
Director, HIV Program
Division of Infectious Diseases
Mayo Clinic


Dr. Tinsay Woretta
Program Director
Transplant Hepatology Fellowship
Assistant Professor of Medicine
John Hopkins University


Dr. Tilahun Yilma
Distinguished Professor of Virology
University of California, Davis


Dr. Seife Yohannes
Vice Chair
Department of Critical Care
Chair
Sepsis Performance Improvement Committee
MedStar Washington Hospital Center