Health and History


                                    የሴቶች  ግርዛት

ይህንን በሚመለከት በዋሽንግተን ዲሲ የሀኪሞቸ ቦርድ ስብሰባ ላይ የቀረበ ሪፖረትና ማሳሳቢያ ማካፈል ተገቢ ነው፡፡  ምክንያቱም በዩናይትድ ሰቴትስ ህግ መሠረት የዚህን አይነት ተግባር መፈፀም ህገ ወጥ ነው፡፡ ይህንን ለማካፈል ወይም ለማስገንዘብ ያሳሰበንም በቀረበው ዘገባ መሠረት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከላይ የተጠቀሰውን ሴቶች ላይ የሚፈፀም ድርጊት ከሚያደርጉ ወገኖች በከፍተኛ ደረጃ ስለሚገኙ ነው፡፡

የአሜሪካ የህግ መምሪያ የሰብአዊ መብቶች ልዪ አቃቢ ህግ ቢሮ መሠረት የሴቶች የፆታ አካላትን  መቁረጥ ፊዴራላዊ ወንጀል ነው

Female Genital Mutilation is a Federal Crime   18 U.S.C. § 116  

በዚህ ዘገባ መሠረት፡

  • ኢትዮጵያ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ዘገባ 74 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የፆታ አካል መቆረጥ የሚያሰከትል ተግባር እንደተደረገባቸው ነው
  • ኤሪትራ ደግሞ በተመሳሳይ ዘገባ መሠረት 89 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ከላይ የተጠቀሰው ተግባር እንደሚደረግባቸው ነው፡፡
  • ሲየራሊዮን 88 በመቶ የሚሆኑ ሲቶች ተመሳሳይ ተግባር አንደሚፈፀምባቸው ነው

በቀረበው ረፖርት ወይም ዘገባ ከላይ የተጠቀሱት አገር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች በሺዎች በሚሆን ቁጥር ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው አንደሚኖሩ ይገልፃል፡፡
በአሜሪካ ህግ መሠረት ሕፃናትን አካል የሚጎዳ ነገር ሲፈፀም እነዚህን ሕፃናት ወይም በሽተኞች የሚያክሙ ወይም የሚረዱ ሰዎች ጉዳቱን ለመንግስት አካላት ሪፖረት እንዲያደርጉ ህግ ያስገድዳል፡፡ ስለዚህ ሀኪሞች ወይም ሌሎች ባለሙያዎች ጉዳት እያዩ ዝም ብለው ማለፍም አይችሉም ማለት ነው፡፡ ይህንን ጉዳት ደግሞ የት ሪፖርት እንደሚያደርጉም አድራሻና ሰልክ ቁጥሮቸ ተሠጥተዋል፡፡
ማንነትዎን ማሳወቅ የለቦትም።.


​ከፌዴራል ህግ በተጨማሪ በየስቴቶች ይህን በሚመለከት ህግ አለ፡፡

እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ሴቶች ላይ የፆታ አካላት ላይ የሚደረግ የመቁረጥ ተግባር ከወንጀል ተቆጥሮ  አስከ አምስት አመት ድረስ በእስራት ያስቀጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እያወቁም ሆነ ሳያውቁ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ሴቶችን ለዚህ ተግባር ከአሜሪካ ውጭ ሌላ ሀገር መላክ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡  በተለምዶ ይህ ተግባር በእንግሊዝኛ vacation cutting ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህንን ተግባር የአሜሪካ ምክር ቤት ህገ ወጥ በማድረጉ ድርጊቱ የሚፈፅሙ ብቻ ሳይሆን ድርጊቱ እንዲፈፀም ተባባሪ የሆኑትን ሰዎች ወንጀለኛ ያደርጋል፡፡

ይህንን ተግባር ለመከላከል የህግ ክፍሉ የሰብኣዊ መብቶች ቢሮ ከተለያዩ የመንግስት አካላቾ ጋር በመተባበር ህጉን የጣሡ ሰዎችን ለፍርድ ያቀርባል፡፡ ይህ ድርጊተ ሲፈፀም የሚያውቁ ሰዎችም እንዲጠቁሙ ወይም ሪፖርት እንዲያደርጉ ያሳስባል፡፡  በዚህ ነገር ላይ ግን ከላይ እንደተጠቀሰው በህክምና ሙያ ላዩ ያሉ ሰዎች ሪፖረት ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው መታወቅ አለበት፡፡ ለዚህ ጉዳይ የስልክና የኢሜይል አድራሻዎች ተሠጥተዋል፡፡

ይህንን በሚመለከት በተለያዪ ቋንቋዎች አማርኛን ጨምሮ የተፃፈ በራሪ ወረቀት አለ፡፡ ወረቀቱ ላይ የተፃፈው መልክት የሚከተለው ነው፡፡

የሰብዓዊ መብቶችና ልዩ ዓቃቤ-ሕግ ክፍል 5863-813-800-1 ስልክ በመደወል ለካትሊን ኦካነር [Kathleen O›Connor] መልእክት ይተው፣ ወይም ወደ ኢሜልዋ HRSPTIPS@USDOJ.GOV መልእክት ይላኩ።በተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ረጋጮችና የጦርነት ወንጀሎች ማእከል በwww.ICE.gov/tips ወይም  በስልክ 6199-872-802-1 ማግኘት ይችላሉ። መረጃውን በሚሰጡበት ጊዜ 

​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic