​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

Health and History

  • The overall cumulative COVID-19 associated hospitalization rate is 40.4 per 100,000,
  • with the highest rates in people 65 years and older (131.6 per 100,000) and 50-64 years (63.7 per 100,000).

  • Hospitalization rates for COVID-19 in adults (18-64 years) are higher than hospitalization rates for influenza at comparable time points* during the past 5 influenza seasons.
  • For people 65 years and older, current COVID-19 hospitalization rates are similar to those observed during comparable time points* during recent high severity influenza seasons.
  • For children (0-17 years), COVID-19 hospitalization rates are much lower than influenza hospitalization rates during recent influenza seasons.

ኢንፍሉዌንዛና ኮሮና


አንዳንድ ሰዎች፣ የኢንፍሉዌንዛ ወረረሽኝ የሚያሰከትለውን አደጋ በትክክል የተገነዘቡና ችግሩንም የተረዱ ሲሆን፣ ከነዚህ መሀል ግን ይህንን ችግር በመጥቀስ፣ ከኮቪድ-19 ጋር በማወዳደር፣ ችላ ወደማለትና ወደ መዘናጋቱ አቅጣጫ መሄድ ብቻ ሳይሆን ሲከራከሩም የታየ ነው፡፡ ይህ ነገር ከዚህ ቀደም በአንዳንድ ጤና ባለሙያተኞችም በኩል የተተንፀባረቀ ነበር፡፡ ያ ሊሆን የቻለበት የራሱ ምክንያት አለው፡፡ ከመጀመሪያው ሳርስ ኮ ቪ2 (ቫይረሱን) አንደቀላል ነገር እንዲታይና ህዝቡ እንዳይረበሽ ሆን ተብሎ በተሠራ ሥርጭትም ነው፡፡

ሁለቱም የሚያሰከትሉትን ነገር እናወዳደር፡፡ አለም አቀፍ የኢንፍሉዌንዛ ሪፖረት ሰሌለ፣ ለማወዳደር፣ የአሜሪካን የኢንፍሉዌንዛ ሪፖርት መጠቀም የግድ ነው፡፡ ስናወዳድር በሶስት መንገድ ይሆናል፡፡

1ኛ. ምን ያህል ሰው ተያዘ፣ ሥርጭቱስ እንዴት ነበር፡፡ ላለመያዝስ አስቀድሞ መከላከል ይቻል ነበር ወይ

2ኛ. የበሽታው ክፋት መለኪያ ከሆኑት አንዱ መመዘኛ፣ ምን ያህል ሰው ወደ ሆስፒታል ገባ፣ እነማንስ ናቸው

3ኛ. ምን ያህል ሰው ሞተ 

የመጀመሪያውን ጥያቄ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ በአብዛኛው፣ ኢንፍሉዌንዛ የመሰለ ህመም፣ (Influneza Like Illess or ILI) ተብሎ ይጠራል፡፡ ሀኪሞች በየሥራ ቦታቸው እምብዛም ወደ ምርመራው ሳይሆን ወደ ህክምናው ነው የሚሄዱት፡፡ መድሐኒትም ስላለ፣ መድሐኒት ይሠጣል፡፡ ቁጥሩ በውል አይታወቅም፡፡ ሥርጭቱን በተመለከተም፣ ብዙ ሰዎች ክትባቱን ሰለሚወስዱ፣ ለኢንፍሉዌንዛ ቢጋለጡም ሳይታመሙ ይቀራሉ፡፡ ከኮቪድ-19 ጋር ሲወዳደር፣ በብዛት እየተጠቁ ያሉት የጤና ባለሙያተኞች፣ ክትባት ሰለሚወስዱ፣ በኢንፍሉዌንዛ የተነሳ ሥርጭት በዝቶ አደጋ ላይ ሲወድቁ አይታይም፡፡ ይህ ግን ያልተለመደ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ወይም አዲስ እሰካልመጣ ድረስ ነው፡፡

ሳርስ ከቪ-2፣ ሥርጭት እንደ ኢንፍሉዌንዛ በተወሰኑ ቦታዎች የተከለለ አለመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በተለይም የአየር ፀባይና የመልክዐ ምድር ሳይወስነው በፈለገበት ቦታ፣ የሰው አግር በዘለቀበት ቦታ ሁሉ እየታየ ነው፡፡ ክትባት የለም፡፡ መድሐኒት የለም፡፡ ብዙ ምርመራ ሰላልተደረግም ቁጥሩ በልክ አይታወቅም፡፡ ይህ በየጊዜው በአሃዝ የሚገለጸው ቁጥር በጣም የተወሰነ ነው፡፡ ሰለዚህ ሰፋቱ ምን ያህል እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ያሰመሰከረው ነገር ቢኖር በአጭር ጊዜ ውስጥ በፍጥነት እንደተዛመተ ነው፡፡

ሁለተኛውን ነጥብ በሚመለከት፣ መረጃ የሚገኝለት ሰለሆነ፣ በደንብ ማወዳደር ይቻላል፡፡ አንድ ነገር መታወስ ያለበት ግን፣ የኢንፍሉዌንዛ ወራት እየቀዘቀዘ የመጣ ሲሆን፣ ሳርስ ኮቪ-2 ግን ገና አየገሰገሰ ነው፡፡ የት ድረስ እንደሚሄድ አዳጋች ነው፡፡ ያም ትክክለኛው የመከላከያ ርምጃ ቢወሰድና ባይወሰድም ብሎ ስሌት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡

የአሜሪካው የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ሰለ ኢንፍሉዌንዛ ያወጣውን ዘገባ እንመልከት፤

 1ኛ. ወደ ዘገባው ስንሄድ፣ በአሜሪካ በየጊዜው ኢንፍሉዌንዛ የመሰለ የሚባል በሽታ መረጃ ይሰበሰባል፣ አንደ ሲዲሰ ገለፃ፣ ይህ መረጃ ከ2600 ከሚሆኑ ህክምና ቦታዎች ነው፡፡ ከጠቅላላው አሜሪካ ደሴቶችንም ጨምሮ ነው፡፡ ኢንፍሉዌንዛ የመሰለ ህመም ሲባል (ትኩሳት ከ100 ዲግሪ ፋራናይት በላይ ወይም 37.8፣ ሳል፣ ጎሮሮ መከርከርን ጨምሮ ከኢንፍሉዌንዛ ውጭ ሌላ ምክንያት የሌለው) የሚጠቀሙበት የፐርሰንት ማወዳደሪያ ለሁሉም ባንድ ላይ ስሌት ማድረግ ሰለማይቻል፣ አገሩ በየአካባቢ ተከፋፍሎ አንደገናም በዕድሜ ተከፋፍሎ ሪፖርቱ ይቀርባል፡፡ ሲዲሲ በየሳምንቱ ነው ይህንን የሚቀርበው፡፡

በዚህ መሠረት ከአካባቢ አንድ አስከ አካባቢ አስር ድረስ በተከፋፈለው ሪፖርት በፐርሰንት ሲገለጥ፣ አነስተኛው ከአካባቢ አስር 1.5 ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ ከአካባቢ ስድስት በ3.8 ፐርሰንት ነው፡፡ ሥርጭቱ ይህንን ይመስላል፡፡ የጠቅላለው የአገሪቱ መሠረታዊ ሥርጭት 2.4 ፐርስነት ነው፡፡ ፐርስንቱ ከአካባቢው የህዝብ ቁጥር በመነሳት ነው የሚሰላው፡፡

2ኛ ሆስፒታል በመግባት

አሰክ አፕሪል 14፣ 2020 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ሪፖርት አሀዝ፣ በ100ሺ ሰዎች ነው የሚገለጠው፣ ያም ከመቶ ሺ ሰዎች ምን ያህል የሚለው እንደገና በዕድሜ ተከፋፍሎ ነው፡፡

ከ0 - 4 አመት              94.1

ከ5 - 17 አመት             24.6

ከ18 - 49 አመት           35.6

ከ50 – 64 አመት          90.2

ከ65 አመት በላይ           179.7

በዚህ ላይ ከፍተኛ ቁጥር የታየበትን የዕድሜ ክልል አስተውሉ፡፡ ኮቪድ የሚለየው ህፃናቱ ላይ አለመበርታቱ ነው፡፡

በኮቪድ በኩል፣ ይህ አይነት ዝርዝር ሰላልደረሰ፣ ሥርጭቱ እየቀጠለ ሰለሆነ ማወዳደር የሚቻል ነገር አይደለም፡፡

 3ኛ. የሞቱ ሰዎች፣ አሁንም በ14ሳመንታት ውስጥ ከሲዲሰ የተሠጠውን ዘገባ በመመልከት፣ ለዚህ ግን፣ ከሲዲሲ የቀረቡትን ግራፍና ምሰሎች መጠቀም የበለጠ ይረዳል፡፡

በአጠቃላይ ትክክለኛ ቁጥር መግለፅ ባይቻልም፣ ከ2010 ጀምሮ እንደ ሲዲሲ ግምት፣ በየአመቱ፣ ከ9 ሚሊዮን እሰከ 45 ሚሊዮን ህምም፣ ከ140ሺ እሰከ 810ሺ ሰዎች ሆስፒታል መግባትና፣ ከ12ሺ አስከ 61ሺ ህይወት ማለፍ አስከትሏል ነው፡፡