አዲስ መጽሐፍ


ኢትዮጵያ ባውሮፓ ዲፕሎማሲ
እንዴት ተረፈች?

GOSH HEALTH


Community health 

education in Amharic 

አማርኛ ማንበብ ለማይችሉ የኢትዮጵያውያን ልጆች ታስቦ፣ የሀገራቸውን ታሪክ እንዲረዱ ስለ አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዝኛ ተፅፎ ለአንባቢ ቀርቧል፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው፣ ቤተዘመድ ለወጣቶች በሥጦታ ሊያበረክቱት የሚገባ መፅሐፍ ነው፡፡ ከኢትዮጵያውያን ውጭም ለሌሎች እንግሊዝኛ አንባቢዎች የሚሆንም ነው፡፡ የውነተኛ ታሪካቸው በመረጃ ተደግፎ ሲቀርብ፣ አፄ ቴዎድሮስን እንኳንስ ኢትዮጵያዊ፣ አፍሪካዊ ሊኮራባቸው የሚገባ ሰው ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም “መቅደላ የቴዎድሮስ ዕጣ” በሚል ርዕስ ጥምር ሥራዎችን (ትርጉምና ስፋትያለው የግርጌ ማስታወሻ) ያቀረቡልን ደ/ር ገበየሁ ተፈሪ፣ ይህንን “Tewodros The Legendary King” የሚል ስለ አፄ ቴዎድሮስ ብዙ ያልተነገሩ ታሪኮችን በማካተት መጠን ያለ ለአንባቢ በሚመች መንገድ የተፃፈ መፅሐፍ ለአንባቢ አቅርበዋል፡፡ መፅሐፉ ለጊዜው በአማዞን ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ  በአውሮፓ  ዲፕሎማሲ እንዴት  ተረፈች በሚል ርዕሰ  በቅርቡ በዶክተር  ገበየሁ  ተፈሪ ተተርጉሞ  የተረቀውና ገበያ ላይ ስለዋለው መጽሐፍ  በበኩሌ መጽሐፉን  ከአነበብኩ በኋላ ጊዜውን ገንዘቡና እውቀቱን በመጠቀም  ስሚወዳት ኢትዮጵያ  ለማዋል  ለአደረገው ከክፍተኛ ጥረት ልባዊ አድናቆቴንና ምስጋናዬን  መግለጽ እወዳለሁ ::
በመቀጠል ይህ በመረጃ የተደገፈ  መጽሐፍ  ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ  ከአለችበት ውጥንቅጥ  ለመውጣት እንደመፍትሔ  በድጋፍ መረጃነት እንዲያገለግል  ለውጭጉዳይ ሚንስትር  ለትምህርት  ሚንስትርና ለሌሎችም  የሚመለከትቸው አካላት  ቢላክ ጥሩ  ነው የሚል  ሀሳብ  ለመሰንዘር  ነዉ ።
ይህ  መጽሐፍ  ኃያላኑ  የአውሮፓ  አገሮች  አፍሪቃን በቅኝ ግዛት ለመቀራመት በ1885 በርሊን  ኮንፈረንስ  ተነስተው  እሽቅድምድም  ይዘው  አንደነበር  በማብራራት  ሩሲያ  ጀርመን  ብሪታኒያ  ጣሊያንና ፈረንሳይ  የነበራቸውን  ፍላጎት ሁሉ  ተቋቁማና ተርፋ  ዛሬ  ላይ መድረሷን  ያስረዳል ። 
ከዚህ የማስቀጠል  የአሁኑ  ትውልድ  ተሸክሞ  ይሆናል 

ቅድመ አድዋ፣ በአድዋ ከዛም በኋላ የተደረገውን የአውሮፓ ተንኮል፣ የምኒልክ ቤተ መንግሥትን የብልጠት አካሄድ በዝርዝር፣ ከዚህ በፊት ለንባባ ባልቀረቡና ሊገኙ በማይችሉ መረጃዎቸ አስደግፎ የቀረበ ፅሁፍ ነው፡፡
ግብፅም ቢሆን፣ ኢትዮጵያ የደከመች ሲመስላት በኢትዮጵያ ላይ የወሰደችውን ርምጃ፣ የአሁን የአባይ ችግር ጥንስስ የተጀመረበትን ሁኔታ በዝርዝር የሚያቀርብ ፅሁፍ ነው፡፡


"ኢንግላንድ ግብፅን ሰለያዘች፣ የግብፅን የህይወት ምንጭና የውሀውን ተፋሰስ ለመቆጣጠር መመኘት አለባት፡፡ እነዚህ ደግሞ በኢትዮጵያ ተራራማ ቦታ ነው የሚገኙት፡፡" 

ከመጽሐፉ የተወሰደ


ከፖለቲካ አቀንቃኝ አስከ ዲፕሎማት ብሎም ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋና ትውልድ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡
ይህንን የሀገሪቱ ወሳኝ ታሪክ ማወቅ የግድም ነው፡፡ ተርጓሚው፣ ኢትዮጵያ እንዴት ተረፈች? በማለት ንዑስ ርዕስ የሠጠው ይህ መጽሐፍ፣ ባነበቡት ሰዎች ደግሞ፣ እንዴት ትተርፋለች? የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡ 

መጽሐፉ በ 02/ 23/ 2020 በዋሽነግተን ዲሲ ተመርቋል፡፡ አራት በሳል ገምጋሚዎች ሰለ መጽሐፉ ያላቸውን አስተያየትና መጽሐፉ ሰላዘለው መልክት ገለፃ አደርገዋል፡፡ ፕሮገራሙ በአቤል ጋሼ መሪነት የተካሄደ ሲሆን፣ በፕሮገራሙ ተሳተፊ የሆኑ ሰዎችም በተለያየ መልክ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ወደፊት ሰለመጽሐፉ የተሠጡ አሰተያየቶችን በዘህ ገፅ እናሰፍራለን፡፡
ባጠቃላይ ግን፣ ማንም ኢትዮጵያዊ ሊያወቀውና ወይም ሊያነበው የሚገባ ጽሁፍ መሆኑን ሁሉም ያነበቡ ሰዎች በምስክርነት የሚገልፁት ነገር ነው፡፡


መጽሐፉን ለማግኘት

  1. በአማዞን
  2. በዋሽንግተን ዲሲ፡ እንጦጦ ገበያ
  3. Omaha, Nebraska

           Danny’s Corner Store
           3301 California street


ስለ መፅሐፉ የተሠጡ አስተያቶች


ሁላችንም እንደምናውቀው ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሪ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ነበሩ፡፡ ገና በካሣነታቸው ዘመን፣ ጥቃትና መገፋትን እንቢ በማለት የፈነኑት ጀግና፣ የተጋፈጣቸውን በሙሉ ድል በማድረግ ለንግሥ የበቁ ናቸው…፡፡ ደ/ር ገበየሁ ላበረከትክልን ቁም ነገር ባለውለታችን ነህና እናመሰግንሃለን፡፡      አርቲስት አለምፀሐይ ወዳጆ

በጊዜው የነበረውን አኗኗር፣ የጦርነቱን ውሎ፣ ወዘተ. በአይነ ኅሊና የሚያስቃኝ መጽሐፍ ስለሆነ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ቢያነቡት ይጠቀሙበታል እላለሁ፡፡ ደ//ር ገበየሁ፣ ሰፋ ያለ መረጃ ለመስጠት ያዘጋጃቸው ማስታወሻዎች ራሳቸውን ችለው አንድ መጽሐፍ ሊወጣቸው ይችል ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡

                 ዶ/ር እንዳላማው አበራ 

ይህን መቅደላ የቴዎድሮስ ዕጣ የተሰኘ መጽሐፍ ከእንግሊዝ ጦር ጋር የተጓዘው ስታሌይ የሚባለው ጋዜጠኛ የዘገበውን ትረካ ወደ አማርኛ በመተርጎም ዶ/ር ገበየሁ ለታሪክ ተመራማሪያን ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የአፄ ቴዎድሮስን ዘመን ለመረዳት የሚፈልግ አንባቢ ታላቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡     

ዶ/ር  አሉላ ፓንክረሰት

ይህ መፅሐፍ አፄ ቴዎድሮስ በግዛት ዘመናቸው የነበረባቸውን ተግዳሮቶችና፣ የእንግሊዝ ጦር የሳቸውን ሠራዊት ለማጥቃት ያደረገውን ከፍተኛ የጦርነት ዝግጅት በዝርዝር ያቀርብልናል፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል መልክዓ ምድር የነበረውን አስደማሚ ውበት በውጭ አገር ጋዜጠኛ አይን በሚገባ ይገልፃል፡፡  

    ፋሲል ጊዮርጊስ፣ አርክቴክት፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር

"መቅደላ የቴዎድሮስ ዕጣ" በአማርኛ  በሚመስጥ መልክ የተዘጋጀ በመሆኑ  ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያነበው ዘንድ እመክራልሁ። ይልቁንም፣ እንደ አንድ ሃገሩንና ወገኑን የሚወድ ኢትዮጵያዊና እንደ የንጉሠ ነገሥት ዓፄ ቴዎድሮስ ቤተሰብ አባልነቴ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪን በእራሴና በቤተሰቦቼ ስም ላመሰግን እወዳለሁ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ። (ለሙሉ አስተያዬት ወስጥ ይመልከቱ)                     አብዩ በለው         

                             

“መቅደላ የቴዎድሮስ ዕጣ” ስለ ቴዎድሮስ ከተፃፉ በርካታ መፃህፍት በተለየ የእንግሊዝ ሠራዊትን ዝግጅት፣ ጉዞና፣ ውጊያ በዝርዝር የሚያሳይ ነው፡፡ መፅሐፉ፣ ለወደፊት ፊልም ሥራዎች ተዝቆ የማያልቅ ጥሬ ሀብት ነው፡፡                                                     ጌትነት እንየው

በዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው መክዘ ከተነሡት ኃያላን መኳንንት አንዱ ናቸው፡፡ የራስ ብሩ ወልደ ገብርኤል ልጅና የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ ሲሆኑ የወገራ አውራጃ ሹም፣ የስሜን አውራጃ ገዥ፣ ልጅ ኢያሱ ከተያዙ በኋላ ደግሞ የንጉሠ ነገሥቱ ጦር አዛዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡


ደጃዝማች አያሌው ብሩ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ወደ ሥልጣን እንዲመጡ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት ሰዎች መካከል ናቸው፡፡ መኢሶ ላይ ከልጅ ኢያሱ ጦር ጋር በተደረገው ጦርነት ተፈሪ መኮንን እንዲያሸንፉ ደጃዝማች አያሌው ከፍ ያለ ሚና ነበራቸው፡፡ ራስ ጉግሣን ለመያዝ አንቺም ላይ በተደረገው ውጊያም የደጃዝማች አያሌው ጀግንነት ወሳኝ ነበር፡፡ እንዲያውም በዚህ ጦርነት ለሚያበረክቱት ውለታ የራስነትን ማዕረግ እንደሚያገኙ ከንጉሥ ተፈሪ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፡፡ በኋላ ግን በአንድ በኩል የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ በመሆናቸው፣ በሌላ በኩልም ከቀድሞዎቹ የዐፄ ምንሊክ ባለ ሥልጣናት ወገን ስለሆኑ ተፈሪ ቃላቸው አጠፉባቸው፡፡


ከሁሉም በላይ ደጃዝማች አያሌውን ያሳዘናቸው በንጉሡ ግብዣ ላይ የነበራቸው ፕሮቶኮል መወሰዱ ነበር፡፡ እንደ ከፍተኛ መኳንንት በንጉሡ ቀኝ በኩል የነበራቸውን የክብር ወንበር ለራስ ደስታ እንዲለቁ መደረጉ ደጃዝማች አያሌውን ‹እጄ አመድ አፋሽ ነው› እንዲሉ አደረጋቸው፡፡ በኋላም ከንጉሥ ተፈሪ ጋር ይበልጥ ተቃቃሩና በቅጣት መልክ አሩሲ ተመደቡ፡፡


ደጃዝማች አያሌው ከንጉሡ ጋር እንደገና ለመስማማት የሞከሩት የጣልያን ጦርነት እየገፋ ሲመጣ ነበር፡፡ ወደ ኤርትራ ድንበር እንዲዘምቱ ትእዛዝ የተሰጣቸው ደጃዝማች(ፊታውራሪ) አያሌው ብሩ መንገድ ላይ ታመሙ፡፡ በኋላም የንጉሡ ሐኪም ስዊድናዊው ዶክተር ሓራልድ ኒስትሮም በአውሮፕላን ተላከላቸው፡፡ በተደረገላቸው ሕክምና ጤናቸው ሲመለስ ረዥም ጉዞ ወደሚጠይቀው የጦር ግንባር ጦራቸውን ይዘው ተጓዙ፡፡ ስዊድናዊው ሐኪምም አብሯቸው ዘመተ፡፡ የጉዞውንም ማስታወሻ በሚገባ ጻፈልን፡፡


ደጃዝማች አያሌው ብሩ ንጉሥ ተፈሪን አምነው ዘመዳቸውን ራስ ጉግሣን ቢዋጉም ቃል የተገባላቸውን የራስነት ማዕረግ ሳያገኙት በመቅረታቸው የጎንደር ሕዝብ

አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ፣ ሰው አማኙ እያለ ዘፍኖላቸዋል፡፡

ዘፈኑም እስከ ዘመናችን ድረስ ደርሷል፡፡


ይህንን ቅሬታቸው ያወቁት ጣልያኖች በተደጋጋሚ ከጎናቸው ሊያሰልፏቸው ሞክረዋል፡፡ ንጉሥ ተፈሪ ደጃዝማች አያሌውን ባለማመናቸው የተነሣ ወደ ጦርነት ሲዘምቱ እንኳን የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ነገር ይሰልሏቸው ነበር፡፡ አብሯቸው እስከ ጦር ግንባር ዘምቶ፣ የኢትዮጵያ ጦር ተሸንፎ ሲመለስም እስከ ደብረ ታቦር አብሯቸው ተጉዞ A memoir of the Italian – Ethiopian war of 1935-36 የተሰኘውን መጽሐፍ እኤአ በ1938 የጻፈው ዶክተር ሐራልድ ኒስትሮም ምናልባት በንጉሡ ላይ ባደረባቸው ቅሬታ ተገፋፍተው ወደ ጣልያኖች ይገቡ እንደሆን ሲጠይቃቸው ‹‹እውነት ነው ንጉሡ በድለውኛል›› አሉ ደጃዝማች አያሌው ‹‹ነገር ግን እኔ ሀገሬን በምንም ያህል ገንዘብ የምከዳ አይደለሁም፤ ጣልያኖች እኔን ይከዳል ብለው ማሰባቸው የሚያሳፍር ነው›› ብለው ነበር መልስ የሰጡት፡፡


አንዳንዴ መንግሥታት፣ ነገሥታት፣ መሪዎች፣ ባለ ሥልጣናት በግለሰቦች፣ በሕዝቦችና በቡድኖች ላይ የሚያደርሱት ግፍና በደል ይኖራል፡፡ ሀገር ግን አትበድልም፡፡ ሀገርና መንግሥት፣ ሀገርና ንጉሥ፣ ሀገርና ፓርቲ፣ ሀገርና መሪ የተለያዩ ናቸው፡፡ እንደ ደጃዝማች አያሌው መሪዎችን ከሀገር መለየት ሲሳን በየዘመናቱ የተነሡ ባለጊዜዎች የሠሩትን ጥፋት፣ በዘመናት ሁሉ ለምትኖር ሀገር ማሸከምን ያመጣል፡፡


ዶክተር ሐራልድ ኒስትሮም የንጉሥ ተፈሪ የግል ሐኪም ሆኖ የተቀጠረው እኤአ በ1927 ነው፡፡ ዶክተር ሐራልድ በቤተ መንግሥትና በቤተ ሳይዳ ሆስፒታል ይሠራ ነበር፡፡ በኋላም ደጃዝማች አያሌው ብሩን ተከትሎ እስከ ጦር ግንባር ድረስ ተጉዟል፡፡ ዶክተር ሐራልድ ጉዞውን በተመለከተ የዛሬ 77 ዓመት ያሳተመው መጽሐፍ በዶክተር ገበየሁ ተፈሪና በደሳለኝ ዓለሙ ‹የተደበቀው ማስተዋሻ› በሚል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ርእስ በጥቅምት 2014(እኤአ) ታትሟል፡፡


አንቡት፤ በሌሎች የታሪክ መጻሕፍት የማናገኛቸውን የጦርነቱን መረጃዎች ከቅርብ የዓይን ምስክር እናነባለን፡፡ ዶክተር ሐራልድ አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገር፣ የሀገሪቱንም ጠባይ የተረዳ ሰው በመሆኑ የሚነግረን ነገር ትኩረት የሚስብ ነው፡፡ በተለይም በመጽሐፉ መጨረሻ የኢትዮጵያ ጦር በማይጨው ዐውደ ውጊያ ለምን ሊሸነፍ እንደቻለ የራሱን አምስት የግምገማ ነጥቦች አስቀምጧል፡፡ ሁላችንም ደግመን ደጋግመን ልናስብባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው፡፡

መልካም ንባብ፡፡