ጤናን በሚመለከት የምክር ርዕሶች

 • ሔፓታይትስ ቢ ምርመራ
 • አለም አቀፍ የዳያቤትስ ፌዲሬሽን ሰለ ጤናማ አመጋገብ ያወጣው ምክር
 • ሔፓተይትስ ሲ ምርመራ
 • ለቱበርኩሎሲስ (ቲቢ) መጋለጥ ምርመራ
 • የሴቶች ግርዛት ህገ ወጥና መዘዙ በአሜሪካ

                    የሴቶች ሀፍረተ ሥጋ አካል ግርዛት ወይም መቁረጥ 

ይህንን በሚመለከት በዋሽንግተን ዲሲ የሀኪሞቸ ቦርድ ስብሰባ ላይ የቀረበ ሪፖረትና ማሳሳቢያ ማካፈል ተገቢ ነው፡፡  ምክንያቱም በዩናይትድ ሰቴትስ ህግ መሠረት የዚህን አይነት ተግባር መፈፀም ህገ ወጥ ነው፡፡ ይህንን ለማካፈል ወይም ለማስገንዘብ ያሳሰበንም በቀረበው ዘገባ መሠረት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከላይ የተጠቀሰውን ሴቶች ላይ የሚፈፀም ድርጊት ከሚያደርጉ ወገኖች በከፍተኛ ደረጃ ስለሚገኙ ነው፡፡

የአሜሪካ የህግ መምሪያ የሰብአዊ መብቶች ልዪ አቃቢ ህግ ቢሮ መሠረት የሴቶች የፆታ አካላትን (ሀፍረተ ሥጋ) መቁረጥ ፊዴራላዊ ወንጀል ነው

Female Genital Mutilation is a Federal Crime       18 U.S.C. § 116  

በዚህ ዘገባ መሠረት፡

 • ኢትዮጵያ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ዘገባ 74 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የፆታ አካል መቆረጥ የሚያሰከትል ተግባር እንደተደረገባቸው ነው
 • ኤሪትራ ደግሞ በተመሳሳይ ዘገባ መሠረት 89 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ከላይ የተጠቀሰው ተግባር እንደሚደረግባቸው ነው፡፡
 • ሲየራሊዮን 88 በመቶ የሚሆኑ ሲቶች ተመሳሳይ ተግባር አንደሚፈፀምባቸው ነው

በቀረበው ረፖርት ወይም ዘገባ ከላይ የተጠቀሱት አገር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች በሺዎች በሚሆን ቁጥር ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው አንደሚኖሩ ይገልፃል፡፡
በአሜሪካ ህግ መሠረት ሕፃናትን አካል የሚጎዳ ነገር ሲፈፀም እነዚህን ሕፃናት ወይም በሽተኞች የሚያክሙ ወይም የሚረዱ ሰዎች ጉዳቱን ለመንግስት አካላት ሪፖረት እንዲያደርጉ ህግ ያስገድዳል፡፡ ስለዚህ ሀኪሞች ወይም ሌሎች ባለሙያዎች ጉዳት እያዩ ዝም ብለው ማለፍም አይችሉም ማለት ነው፡፡ ይህንን ጉዳት ደግሞ የት ሪፖርት እንደሚያደርጉም አድራሻና ሰልክ ቁጥሮቸ ተሠጥተዋል፡፡

ከፌዴራል ህግ በተጨማሪ በየስቴቶች ይህን በሚመለከት ህግ አለ፡፡

እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ሴቶች ላይ የፆታ አካላት ላይ የሚደረግ የመቁረጥ ተግባር ከወንጀል ተቆጥሮ  አስከ አምስት አመት ድረስ በእስራት ያስቀጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እያወቁም ሆነ ሳያውቁ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ሴቶችን ለዚህ ተግባር ከአሜሪካ ውጭ ሌላ ሀገር መላክ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡  በተለምዶ ይህ ተግባር በእንግሊዝኛ vacation cutting ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህንን ተግባር የአሜሪካ ምክር ቤት ህገ ወጥ በማድረጉ ድርጊቱ የሚፈፅሙ ብቻ ሳይሆን ድርጊቱ እንዲፈፀም ተባባሪ የሆኑትን ሰዎች ወንጀለኛ ያደርጋል፡፡

ይህንን ተግባር ለመከላከል የህግ ክፍሉ የሰብኣዊ መብቶች ቢሮ ከተለያዩ የመንግስት አካላቾ ጋር በመተባበር ህጉን የጣሡ ሰዎችን ለፍርድ ያቀርባል፡፡ ይህ ድርጊተ ሲፈፀም የሚያውቁ ሰዎችም እንዲጠቁሙ ወይም ሪፖርት እንዲያደርጉ ያሳስባል፡፡  በዚህ ነገር ላይ ግን ከላይ እንደተጠቀሰው በህክምና ሙያ ላዩ ያሉ ሰዎች ሪፖረት ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው መታወቅ አለበት፡፡ ለዚህ ጉዳይ የስልክና የኢሜይል አድራሻዎች ተሠጥተዋል፡፡

ይህንን በሚመለከት በተለያዪ ቋንቋዎች አማርኛን ጨምሮ የተፃፈ በራሪ ወረቀት አለ፡፡ ወረቀቱ ላይ የተፃፈው መልክት የሚከተለው ነው፡፡

የሰብዓዊ መብቶችና ልዩ ዓቃቤ-ሕግ ክፍል 5863-813-800-1 ስልክ በመደወል ለካትሊን ኦካነር [Kathleen O›Connor] መልእክት ይተው፣ ወይም ወደ ኢሜልዋ HRSPTIPS@USDOJ.GOV መልእክት ይላኩ።በተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ረጋጮችና የጦርነት ወንጀሎች ማእከል በwww.ICE.gov/tips ወይም  በስልክ 6199-872-802-1 ማግኘት ይችላሉ። መረጃውን በሚሰጡበት ጊዜ ማንነትዎን ማሳወቅ የለቦትም።.

አለም አቀፍ የዳያቤትስ ፌዲሬሽን ሰለ ጤናማ አመጋገብ ያወጣው ምክር

ይህ ምክር ስኳር በሽታን ለመከላከልም ታስቦ ነው፡፡

 1. መጠጥን በተመለከተ፡ ከፍራፍሬ ጭማቂ፣ ከሶዳ (ለስላሳ መጠጥ) እና ከሌሎችም በስኳር ከጣፈጡ መጠጦች ፋንታ ውሀ፣ ቡና፣ ሻይ ይምረጡ
 2. በቀን ከተቻለ ሶስት ጊዜ አትክልቶችና ያም አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎችን ይመገቡ
 3. ከተቻለ በቀን ሶሰት ጊዜ የሚሆን አዲስ (fresh) ፍራፍሬዎች ይመገቡ
 4. መክሰስ ቢጤ ካስፈለገም፣ እንደ ኦቾሎኒ፣ የፍራፍሬ ቁራጭ ወይም በሰኳር ያልጣፈጠ እርጎ
 5. የአልኮል መጠን ቢሆን በቀን ከሁለት መጠጥ በላይ አይጠጡ
 6. ሥጋን በተመለከተ፣ በፋብሪካ ከተዘጋጀ ሥጋ ይልቅ የተመተረ ወይም የተቆረጠ የከብት ሥጋ፣ የዶሮ ሥጋ እና የአሳ ዝርያዎችን ይመገቡ
 7. ዳቦ ላይ የሚቀቡ ነገሮችን በሚመለከት በቾኮሌት የተቀመመ ማባያ ይልቅ፣ የኦቾሎኒ ወይም ለውዝ (Peanut butter) ይጠቀሙ
 8. ከነጭ ሩዝ፣ ነጭ ዳቦና ነጭ ፓስታ ከመመገብ Whole grain bread, Brown rice, or whole grain pasta, ይምረጡ
 9. ዘይትን በሚመለከት Unsaturated oil (የወይራ ዘይት olive oil, canola oil, sunflower oil) እንጂ ቅቤ፣ አይብ፣ የእንስሳት ጮማ፣ የኮኮናት ዘይት፣ ወይም Palm Oil) አይጠቀሙ


የሰውነት እንቅስቃሴን በተመለከተ የአለም የጤና ድርጅት ለተለያዬ ዕድሜ ላላቸው ሰዎች ያወጣው ምክር


 • ዕድሜያቸው ከ 5- 17 አመታት ውስጥ ያሉ ልጆች፣ በቀን ቢያንስ የ60 ደቂቃ ጠንከር ያለ የሰውነት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ


 • አዋቂዎች ከ18 – 64 ዕድሜ ክልል የሚገኙ ደግሞ በሳምንት ውስጥ፡ ከ150 ደቂቃዎች ያላነሰ ጠንከር ያለ የሰውነት እንቅስቃሴ ለምሳሌ (ፈጠን ያሉ እርምጃዎች፣ ሶምሶማ ሩጫ፣ ወይም አትክልት ሥራ) እነዚህ ባንድ ቀን ሳይሆን በሳምንቱ ውስጥ በተለያዩ ቀናት መሆን አለባቸው፡፡ ከልሆነም ቢያንስ ቢያንሰ በሳምንት ውስጥ 75 ደቂቃዎች የመሆን ጠንከር ያለ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖባቸዋል፡፡ ጠንከር ያለ ሲባል አንግዲህ በአብዛኛው ጊዜ ላብ እስከሚወጣቸው ድረስ የሚሆን ለማለት ነው፡፡


 • በዕድሜ ለበለፀጉ አዋቂዎች ደግሞ ተመሳሳይ ለሆነ ጊዜ ተመሳሳይ የሰውነት እንቅሰቃሴ ይመከራል ነገር ግን በዚህ ዕድሜ ክልል ላሉ ሰዎች ግን እንደ ችሎታቸው መጠን ጡንቻ የሚያጠነክሩ እንቅስቃሴዎች ጋር ተደባልቆ መሆን አለበት፡፡