​ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ


አዘጋጅና አቅራቢ 
ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

Health and History

ለመሆኑ የደም ግፊትዎ መጠን ምን ያህል ነው?

በአዲሱ መመሪያ መሠረት የደም ግፊት መጠን (Blood pressure) ደረጃ ይህን ይመስላል
የላይኛው (systolic) 130ና ከዛ በላይ ከሆነ ጤናማ አይደለም፡፡ የታችኛው ደግሞ (diastolic) 80ና ከዛ በላይ ከሆነ ጤናማ አይደለም፡፡
በደረጃ ሲመደብ 
የላይኛው Systolic በ120 -129 ና የታችኛው diastolic ከ80 በታች ቢሆን እንኳን ይህ ሁኔታ ከፍ ያለ የደም ግፊት ይባላል፡፡


ደረጃ 1 (Stage 1) የሚባለው የላይኛው systolic ከ130 -139 የታችኛው diastolicደግሞ ከ80 -90


ደረጃ 2(Stage 2)  የሚባለው የላይኛው systolic  ከ140 በላይ የታችኛው diastolic ደግሞ ከ90 በላይ ሲሆን


የደም ግፊት አደጋ (Hypertension Crisis) የሚባለው ደግሞ የላይኛው ከ180 በላይ የታችኛው ደግሞ ከ120 በላይ ሲሆን ነው፡፡ 


እዚህ ላይ አንድ መጠቀስ የሚገባው ነገር አለ፡፡ የደም ግፊት መጠን በዘፈቀደ የሚለካ አይደለም፡፡ የራሱ አለካክ አለው፡፡ አለዛ በስህተት ቁጥሩ ወደ ላይ ከፍ ሊል ሰለሚችል ያለ አግባብ ለተጨማሪ መድሀኒት መጋለጥም ይመጣል፡፡ 

ሰለ ደም ግፊት አለካክ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡

  • ከልብስ ላይ የደም ግፊት መጠን መለካት በቁጥር 50 mmhg ድረስ ሊጨምር ይችላል
  • የደም ግፊት ከመለካቱ በፊት ተለኪው ሰው ለአምስት ደቂቃ ረጋ ባለ ሁኔታ አረፍ ማለት አለበት አለዛ መጠኑ ሊጨምር ይችላል፡፡
  • የደም ግፊት መለኪያ ማሰሪያው አነስ ወይም ጠበብ ያለ ከሆነ የደም ግፊቱ በ 10 ድረስ ሊጨምር ይችላል
  • ደም ግፊትዎ ሲለካ ወሬ እያወሩ ከሆነ፣ ማዳመጥ ብቻ ራሱ 10 mmhg ይጨምራል፡፡ 


አስተውላችሁ ከሆነ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ስህተቶች በአብዛኛው ጊዜ የሚደረጉ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት በስህተት የደም ግፊቱ መጠን ከፍ እንዳለ ተደርጎ ሊዘገብ ይችላል፡፡ በተጨማሪም በዚህ የስህተት አለካክ ምክንያት በሽታው የሌለበት ሰው እንዳለበት ተደርጎ ሊነገረው ይችላል፡፡ የሚወጡት መመሪያዎችም የተመረኮዙት ትክክለኛ በሆነ የደም ግፊት አለካክ ላይ መሆኑ መታወስ አለበት፡፡ 

ወደ ህክምና ስንመለስ ደረጃ 1 የደም ግፊት መጠን ያለባቸው ሰዎች ሌላ ተደራቢ በሽታ ከሌለባቸው በስተቀር መድሐኒት መጀመርም አያስፈልጋቸውም፡፡ እነዚህ ተደራቢ በሽታዎች የሚባሉት፣ የልብ ድካም፣ የስኳር በሽታ፣ የኩላሊት በሽታና ሌሎች ከደም ዝውውር ጋር የተያያዙ በሽታዎቸ ካሉ ነው፡፡

ሌላው ነጥብ፣ አሁን ለጊዜው ጉዳት ሊያስከትል ይችል ይሆናል የሚባል ጥናት ቢታይም፡፡ በአጠራር (White coat hypertension፣ ጎሽ ድረ ገፅን Goshhealth.org ይጎብኙ) የሚባለው፣ ሰዎች ወደ ህክምና ቦታ ሲሄዱ ደም ግፊታቸው ከመጠን በላይ ከፍ ብሎ የሚታይበት ነገር ግን በቤታቸው ሲሆኑ ጤናማ መጠን ላይ ሆኖ ሰለሚገኝበት ሁኔታ በማሰታወስ፣ ሰዎች ቤታቸው ቁጭ ብለው አረፍ ብለው ደም ግፊታቸውን እንዲለኩ ማድረግ ይመከራል፡፡

የደም ግፊት በዕድሜ በሰውነት ክብደት መጨመረም ሊቀያየር ስለሚችል በየጊዜው መለካት አስፈላጊ ነው፡፡ በቤተሰብ ደረጃም የሚታይ ስለሆነ፣ ደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ቤተሰቦች እንዲለኩ እንመክራለን፡፡ ዋናው አስፈሪው ነገር፣ የደም ግፊት መጠኑ ከፍ ብሎ ምንም ምልክት ሳይሠጥ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ሰለሆነ ሰዎች በዚህ ከፍ ባለው የደም ግፊት ምክንያት ኩላሊትና ሌላም የሰውነት ክፍሎች ላይ አደጋ ከመድረሱ በፊት በጊዜ ማውቅ፣ በምግብና በመድሐኒት ከፍታውን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው፡፡ የራሰዎን ደም ግፊት እሰካልተለኩ ድረስ ጤናማ መሆኑን ሰለማያውቁ ደም ግፊትዎን ይለኩ፡፡

 ለሌሎች ያካፍሉ፡፡

የደም ግፊት ህክምና አዲስ መመሪያ
 
ስለ ደም ግፊት (Hypertension) በተለምዶ በሀገር ቤት ደም ብዛት ሰለሚባል በሽታ አብዛኛው ሰው መጠነኛ ግንዛቤ እንደሚኖረው ነው፡፡ ነገር ግን በደም ግፊት ምክንያት የሚደርሰውን የሰውነት ጉዳትና ይህይወት ህልፈት በመመልከት ሰለዚህ ችግር ተደጋጋሚ ግንዛቤ መስጠት ተገቢ ነው፡፡  ይህ በሽታ የደም ግፊት መጠን ከጤናማ በላይ ሲሆን እንደ በሽታ የሚቆጠረው፡፡ የደም ግፊታቸው ከጤናማ መጠን በላይ የሆኑ ሰዎች ደግም መድሃኒት መጀመር እንዳለባቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን መድሀኒት የሚጀመርበት የደም ግፊት መጠን ለተለያዩ ሰዎች የተለያዪ ነው የሚሆነው፡፡ በተለይም በእድሜ በኩልና ሌሎች ተደራቢ በሽታዎች ባሉባቸው ሰዎች ላይ፡፡
እንደሚታወቀው የደም ግፊት ሲለካ ሁለት ቁጥሮች አሉ በአንግሊዝኛ (systolic ) የላይኛው እና (diastolic ) የታችኛው ቁጥር፡፡ እነዚህ ቁጥሮች አንዱ ወይም ሁለቱ ከመጠን በላይ ሲሆኑ የደም ግፊት አለ ይባላል፡፡ ማሰተዋል ያለብን እነዚህ ቁጥሮች ከመጠን በላይ ሲሆኑ ምንም የህመም ስሜት ወይም ምልክት ላይኖር እንደሚችል ነው፡፡ ዋናው ችግር ይህ የደም ግፊት በጊዜ ካልታወቀ ሊያሰክትል የሚችላቸው የተላየዪ በሽታዎች መኖራቸው ነው፡፡ ዋናዎች ችግሮች

  • ስተሮክ (stroke) የነርቭ ምች(ከህይወት ማለፍ ጀምሮ የሰውነትን ክፍል ሽባ በማድረግ የሚታወቅ
  • ድንገተኛ የልብ ህመም (Heart attack) በሰሜን አሜሪካ ለሕይወት ህልፈት ዋነኛው ምክንያት
  • የኩላሊት መድከም (Kidney failure) ለኩላሊት መድከም ዋና ምክንያቶች አንዱ


ስለዚህ እነዚህን በሽታዎች ለመከላከል የህመም ስሜትም ባይኖር የደም ግፊትን በመድሀኒት አማካኝነት ጤናማ ደረጃ ወይም መጠን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

የደም ግፊትዎን (Blood Pressure) መጠን ያውቃሉ ወይ?

በትክክል መለካቱንስ ያወቃሉ ወይ?
 5/26/2018 
በየጊዜው ጤናማ የሆነው የደም ግፊት መጠን ወይም ቁጥር ሲቀየር ይታያል፡፡ ይህም የሚሆነው ጤናማ ያልሆነው የደም ግፊት መጠን በሰውነት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እየታዬ ነው፡፡ በህዳር 2017 የአሜሪካ የልብ ሀኪሞች ማሕበር ጤናማ የደም ግፊት መጠን ቁጥርን በሚመለከት አዲስ መመሪያ አውጥቷል፡፡ ብዙ ጊዜ ጥያቄው እነዚህ መመሪያዎች የሚወጡት በአሜሪካ ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ከዛ ውጭ ለሚኖሩ ሰዎች ላይስ እንዴት ነው የሚለው ነው፡፡ ሆኖም የደም ግፊትን በተመለከተ ብዙም መራራቅ ላይኖር ይችላል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያም ቢሆን በደም ግፊት የተነሳ የህይወት እልፈት፣ ኩላሊት መድከም፣ ስትሮክ የመሳሰሉት በብዛት የሚታዩ ነገሮች በመሆናቸው እንዲህ አይነቱ መመሪያ ሲወጣ አንባቢ በአትኩሮት ሊያሰተውለው የሚገባ ነገር ነው፡፡