የበሽታው ምልክቶች
ለባክቴሪያው ከተጋለጡ ከሁለት አስከ አስር ቀናት በኋላ ሰዎች ምልክትና ሰሜት ይኖራቸዋል፡፡ እነሱም፤

በመጀመሪያ የሚሰሙት ምልክቶች

  • ትኩሳት እሰከ 104 ዲግሪ፣ ወይም 40 ሲንቲ ግሬድ
  • ብርድ ብርድ ስሜት
  • ራስ ምታት
  • የቁርጥማት ስሜት


ከሁለት ወይም ከሶሰት ቀናት በኋላ ደግሞ የሚከተሉት ስሜትና ምልክቶች ይከሰታሉ፡፡
ሳል፣ አክታ ያለው አንዳንዴም በአክታው ደም ይታይበታል
የትንፋሽ ማጠር ስሜት
የደረት ህመም
ማቅለሽለሽ፣ ትውኪያ፣ ተቅማጥ፣
እየበረታ ሲሄድ ደግሞ የአእምሮ ለውጥና የመደናገር ምልክቶችን ጨምሮ ይከሰታል፡፡
በሽታው ወደ ከፋ ደረጃ ሲደርስ፣ የትንፋሽ ማቆም ወይም መድከም፣ የኩላሊት መድከምና፣ የደም ዝውውርን ጨምሮ ጠቅላላ ሰውነት መደከም ወይም ሾክ ውስጥ መግባትን ይጨምራል፡፡

ለበሽታው መጋለጥ ምክንያት የሚሆኑ ቦታዎች ወይም ሁኔታዎች፡፡

ዋናው እንግዲህ ይህ ባክቴሪያ ያደገበትን ውሀ መጋለጥ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእብዛኛው አካለት ለመታጠብ ሻወር በመውሰድ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን፣ ከዚህ ቀደም የተዘገቡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ እነሱም፤

የገላ መታጠቢያ የሞቁ ገንዳዎች ወይም የውሃ መታሻዎቸ፣ የመዝናኛ መርከቦች
በየግሮሰሪዎች በአትክልቶች አካባቢ የሚረጩ የውሃ ጠብታዎች
ከአየር ማቀዝቀዣ (Air conditioner) የሚወጡ የውሃ ገንዳዎች
ለጌጥ ወይም ለታይታ የሚታዩ ውሃ የሚረጩ ቅርፆች
የመዋኛ ገንዳዎች
ሰውነት ህክምና Physical therapy መገልገያ መሣሪያዎች
በሆሰፒታሎች፣ በሆቴሎችና ህሙማን መሰንበቻ ስፍራዎች የውሃ መተላለፊያ መስመሮች

ይህንን በሽታ ለመከላከል ዋናው መንገድ የውሀ መስመሮችንና ውሃ የሚከማችባቸው መገልገያዎችን ማፅዳት ነው፡፡ በየመኖሪያ ቤት የሚገኙ ለጌጥ የምናስቀምጣቸው ውሃ የሚረጩ ነገሮችን በየጊዜው ማፅዳት፤ በሰዎች በኩል ከመጣ ግን ሲጋራ አለማጨስ ዋናው መንገድ ነው፡፡ በአጫሾች ላይ በሽታው ይበረታል፡፡

ሕክምና
በሽታው አንደሌሎች አይነቶች የሳምባ ምች በሽታዎቸ ምርመራ ይደረጋል፡፡ በሽንት ምርመራ በሚደረግ የላቦራቶሪ ምርመራ የሳምባ ምቹ በዚህ ባክቴሪያ ምክንያት መሆኑን መለየት ይቻላል፡፡ ሌሎቸ እንደ ደረት ራጅ (ኤክስ ሬይ)፣ ካት ሰካን የመሳሳሉት የበሽታውን መጠን ለመረዳት ያስችላሉ፡፡

ለዚህ በሽታ ሕክምና የሚሠጡ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ለማንኛው ከላይ ከተዘረዘሩት መጋለጫ መንገዶች ተጋልጠው ከሆነ ለሀኪምዎ መንገር አስፈላጊ ነው፡፡ መንገድ ወጥተው ከሆነ፣ በሆቴሎች አርፈው ከሆነም ለሀኪም መንገር አስፈላጊ ነው፡፡


የአትላንታ ሼራተንን ሆቴልን ያዘጋው ተላላፊ የሳምባ ምች በሽታ

በጁላይ 15 የአትላንታው ሸራተን ሆቴል እንግዶቹን በማስወጣት መዘጋቱን በተለያዩ የመገናኛ መሠራጫዎች ተገልፆአል፡፡ ይህ ደግሞ፣ ጊዜው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵውያን ሰፖርት ውድድር በተካሄደ በሳምንቱ ነበር፡፡ አንደምናስታወሰው፣ ኢትዮጵያውያኑ አትላንታ ከተማን አጥለቅለቃውት እንደነበር ይታወሳል፡፡ አንደ ጆርጂያ የጤና ቢሮ ገለፃ፣ ከዚህ ሳምባ ምች በሽታ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው የሞተ ሲሆን፣ ከአስራ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተለክፈዋል የሚባል ግምት አለ፡፡ ሆቴሉ በሩን የዘጋው በመልካም ፈቃድ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቷል፡፡ አንደተለመደው ጠበቃ ጉዳዩን ጀምሯል፡፡ ጠበቃው እንደሚሉት ከሆነ ቁጥራቸው ከመቶ በላይ የሆኑ ሰዎች ሳይጋለጡ እንዳለልቀረ ነው፡፡ የጤና ቢሮው፣ ወደ 63 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ክትትል እያደረገ ነው፡፡ በሽታው ሌጂነርስ ዲዚዝ Legionnaires Disease ይባለል፡፡ የሚመጣው ሌጂነላ ኒሞፊሊያ Leginonella Pneumophilia በሚባል ባክቴሪያ ነው፡፡ ሰለዚህ በሽታ በዚህ አጋጣሚ ለአንባቢያን ትምህርትና ምክር ይቀርባል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም፣ በአትላንታ ሼራተን ሆቴል ተሰተናገድው የነበሩ ሰዎች ካሉም ይህንን ሁኔታ ቢከታተሉ ጥሩ ነው የሚል ሃሳብ አናቀርባልን፡፡ ይህ መረጃ፣ ሄልዮ በተባለ የተላላፊ በሽታዎች መጋዚን የቀረበ ነው፡፡ በሽታው የሚከሰተው፣ ለባክቴሪያው ከተጋለጡ ከሁለት አስከ አስር ቀናት በኋላ መሆኑን ግንዛቤ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

ወደ ሌጂነላ ኒሞንያ ወይም ሌጂነርስ በሸታ ስንመለስ፣
ይህ በሽታ እንደ አሜሪካው የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል CDC፣ በየጊዜው በቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ ከ2010 እስከ 2014 ባለው ጊዜ በአራት ዕጥፍ እንደጨመረ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በአሜሪካ ብቻ ነው፡፡ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች፣ ከአስሩ አንዱ ህይወታቸው እንደሚያልፍም ተዘግቧል፡፡

በሽታውን የሚያስከትለው ባክቴሪያ በተፈጥሮ በውሃ ውስጥ ይኖራል፡፡ ነገር ግን በህንፃዎች የውሃ መስመሮች ውስጥ ሲያድግና ሰዎች ለባክቴርያው ሲጋለጡ፣ የሳምባ ምች PNEUMONIA ወረረሽኝ ያስከትላል፡፡ ሰዎች ለዚህ ባክቴሪያ የሚጋለጡት የውሃውን ብናኞች ከአየር ጋር ወደ ሳምባቸው ሲያስገቡ ነው፡፡ በትንፋሽ ማለት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ፣ ይህ ባክቴሪያ ያለበትን ውሃ በመጠጣት ነው፡፡ ከዚህ በውሃ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ሥፍራዎቸ ሰዎች የተለከፉ መሆናቸውን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ይህ ባክቴሪያ የሚያስከትላቸው በሽታዎች ሁለት አይነት ሲሆኑ፣ አንደኛው ፖንቲያክ ፊቨር የሚባል ቀለል ያለ በሽታ ሲሆን፣ ሌላው ግን ከላይ እንደተጠቀሰው ሌጂኔሎሲስ ወይም ለጂነርስ ዲዚዝ ይባላል፡፡ ይህ በሽታ ዘወትር ከሚከሰቱት የሳምባ ምች በሽታዎች የተለየ ሆኖ፣ በጣም አስጊ የሆነ የሳምባ ምች በሽታ ያስከትላል፡፡ በሽታው ከሰው ወደ ሰው አይሸጋገርም፡፡ ተመስገን፡፡ ከላይ አንደተገለፀው በባክቴሪያው የተለከፈ ውሃን ወይም ጠብታን በሚተነፍሱበት ጊዜ ወደ ሳምባቸው ያሰገቡ ሰዎች ለበሽታው ይጋለጣሉ፡፡ ከሚጋለጡ ሰዎች መሀል በሽታው በቀላሉ ሊከስትባቸው የሚችሉ ሰዎች አሉ፣ እነሱም በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ ሲጋራ አጫሾችና፣ በተለያዩ ምክንያቶች የሰውነት የበሽታ መከላከያ አቅማቸው የደከሙ፣ ዘላቂ ወይም ሥር የሰደደ የሳምባ በሽታ(Emphysema) ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ በሽታ ሌጂነርስ ዲዚዝ የተባለው፣ እኤአ በ1976፣ በፊላደልፊያ ከተማ በሌጂነርስ ኮንቬንሽን ወይም ስብሰባ በአንድ ሆቴል ሰዎች በብዛት በዚህ በሽታ ተለክፈው ከተገኙ በኋላ ነው፡፡

ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ
አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic