ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ
አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

የህንዱ ኮሮና ቫይረሰ አሳሳቢ ነው ተባለ

በቀን 25 ሺ ሰዎች እየሞቱ ነው ተብሎ ይገመታል

ከዚህ ቀደም በጎሽ ድረ ገፅ ሆነ በሌላ መንገድ ቸግር ሊሆን ይችላል በማለት በተደጋጋሞ የምጠቅሰው ነገር ቢኖር፣ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት በጨመረ ቁጥር ቫይረሱ አዳዲስ ዝርያዎችን መፍጠር መቻሉ ነው፡፡ አዲስ የቫይረሱ ዝርያዎች ሲፈጠሩ በሁሉት ምድብ ይከፈላሉ፡፡ አዲስ የመጡት አትኩሮት የሚሠጣቸው የሚባሉ በአንድ ወገን ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ አሳሳቢ ዝርያዎች የሚባሉ በሌላ ወገን ይመደባሉ፡፡ እንደ አለም የጤና ደርጅት በአሀኑ ጊዜ አስር የሚሆኑ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች በአሳሳቢነት ደረጃ የተመደቡ አሉ፡፡

አሳሳቢ እንዲባሉ የሚያደርጋቸው አዲስ ዝርያ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ በሚያሳዩት ባህሪ ነው፡፡ የመጀመሪያው የባህሪ ለውጥ ቀድሞ ከታየው የኮሮና ቫይረስ በበለጠ ከሰው ወደ ሰው የመሻገር ችሎታቸው ሲጨምር ነው፡፡ ሁለተኛና ሶስተኛ ባህሪዎች ደግሞ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ከድሮው በበለጠ ለከፋ ህመም መዳረግና በዚህም ምክንያት የመግደል ችሎታ መጨመር ነው፡፡

አዲስ ቫይረሶች የአካላቸው ክፍል ከሆነው ወሳኝ ፕሮቲን ላይ የዘር ሀረግ ለውጥ ሲያደርጉ ፕሮቲኑን የመለወጥ ሁኔታ ሰለሚከተል በዘር ደረጃ ከቀደመው ቫይረስ ይለያሉ፡፡ አንዳንድ ቫይረሶች ደግሞ አንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን የተለያያ ተጨማሪ ቦታዎች ለውጥ በማድረግ ለየት ያለ ፕሮቲን ይኖራቸዋል፡፡

የህንዱ ቫይረስ አንድ ብቻ ሳይሆን ሶስት ለውጥ ቦታ ሰላለው (Triple mutant) ብለው እየጠሩት ነው፡፡ በኮድ ቁጥሩ B.1.617 ተብሎ የሚጠራው ይህ አዲስ ዝርያ፣ በአለም የጤና ድርጅት በኩል አሳሳቢ ከሚባሉ ቫይሶች ወገን ተመድቧል፡፡ እነሱ አሳሳቢ ነው ሲሉ፣ ቫይረሱ ከህንድ ወጥቶ ሌላ ቦታ ሊዛመት ይችላል በሚል ስጋት ነው፡፡ ለነገሩማ በእንግሊዝ አገር መጀመሪያ የታየው ቫይረስ አሁን አለምን እየተቆጣጠረ በአንዳንድ አገሮች ለአራተኛ ዙር ማዕበል ወረርሽኝ አብቅቷቸዋል፡፡

የህንዱ ቫይረስ በፍጥነት መሠራጨት መቻሉ ተረጋግጧል፡፡ የሳይንስና የመረጃ ጉዳይ ሰለሆነ በሽታ በማምጣት ጉልበት መጨመሩና ደግሞ የመግደል ችሎታው መጨመሩ በጥናት ይቅረብ በማለት ቁርጥ ያላ ሀሳብ ከመስጠት ገሸሽ ብለዋል፡፡

ለተከታተለ ሰው ግን፣ በህንድ በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥታቸው በሚሰጠው ሪፖርት በቀን አራት ሺ ሰው እየሞተ ነው ይላሉ፡፡ ያ ግን ከሚታወቀው፣ ሆሰፒታል ገብቶ በምረመራ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ለተረጋገጠ ሰው ነው፡፡ ሰለዚህ ይህ አራት ሺ ቁጥር ዝቅተኛው ነው ማለት ነው፡፡ በሜድያ፣ ዝርያቸው ህንዳዊ የሆኑ ግን የአሜሪካ ፕሮፌሰር እንደሚሉት ከሆነ፣ አራት ሺ ሞት በየቀኑ የሚባለው ትክከለኛ ጣራው አይደለም ይሉና ቀጥለውም የሳቸው ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ትንተና ወይም ጥናት፣ በህንድ በአሁኑ ጊዜ በቀን 25ሺ ሰው እየሞተ እንደሆን ይናገራሉ፡፡ ከዚህ ቀደም እንደገለፅኩላችሁ፤ በየቀኑ የሚሞተው ሰው ቁጥር ይታወቃል፡፡ ሰለዚህ በሳቸው አባባል በየቀኑ ምናልባትም ከ25ሺ ሰዎች በላይ እየሞቱ ነው፡፡ ጥያቄው ታዲያ ከነዚህ ውስጥ ምን ያህሉ በኮቪድ ምክንያት ሞተ ነው፡፡ ትርፍ ሞት ወደሚባለው የቅመራ መንገድ እየወሰድኳችሁ ነው፡፡

እንግዲህ በኢትዮጵያም ቢሆን፣ የሚሞተውን ሰው ቀጥር በቀላሉ ማወቅ ይቻላል፡፡ በተለይም እምነት ቤቶች በየደብሩ አለዚያም በመስጊድ አማካኝነት በየቀኑ የሚሞተው ሰው ቁጥር አላቸው፡፡ ያ የሚሞተው ሰው ሁሉ ለኮቪድ ምርመራ ቀርቶ ሆስፒልም ያልገባ ነው፡፡ ትርፍ ሞት ማለት አምናና ታች አምና በዚህ ወቅት ሲሞት የነበረው ሰው ቁጥር ግምቱ አለ፡፡ አሁን ግን ሰው በብዛት ከሚገመተው በላይ እየሞተ ነው ከተባለ፡፡ በብዛት ከሚገባው በላይ እየሞተ ያለው ሰው በምን ምክንያት ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ነው፡፡ በወቅቱ ሰው መግደል የሚችል ወረርሽኝ ባለበት ሰአት ሌላ የሞት ምክንያት ቢኖርም ይህን ያህል ሰው እንዲሞት የሚያደርገው እንግዲህ ኮቪድ መሆኑ ነው፡፡

አዲስ ቫይረሶች ሲከሰቱ ሌላ ፍራቻ እንዳለም መዘንጋት የለብንም፣ እነሱም ክትባት የማምለጥ ችሎታና ያሉትን መድሀኒቶች የማምለጥ ችሎታዎች ናቸው፡፡ በክትባት ከመጣ የደቡብ አፍሪካ ዝርያው አሁን በአገልግሎት ላይ ካሉ የኮቪድ ክትባቶች አንደኛውን ከጥቅም ውጭ ሰላደረገው፣ ያ ክትባት በደቡብ አፍሪካ እንዳይሠጥ ተደርጓል፡፡

ታዲያ ከዚህ መማር የሚገባን ነገር ቢኖር፣ ወረርሽኙን በክትባት ብቻ ማምለጥ እንደማይቻል ነው፡፡ ያውም በቂ የሆነ የህብረተሰቡ ቁጥር ባልተከተበበት ሁኔታ፡፡

ሌላው ችግር በሌሎቹ ቫይረሶች እንደታየው በህንድም ይሁን በሌላ አገር የተከሰተው ቫይረስ አገሪቱ ውስጥ ዘልቆ መግባት አንደሚችል ሰለሚታወቅ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ግን፣ ሥርጭቱን ለመቆጣጠር የመከላከያ ዘዴዎች  ተግባራዊ ካልሆኑ፣ ቫይረሱ ራሱ በኢትዮጵያ ውስጥ የራሱን አዲስ ዝርያ መፍጠር እንደሚችል ማወቅ ነው፡፡ ይህንን ለማወቅ፣ ጀኖሚክ ጥናት የሚባል፣ የቫየረሱን የዘር ሀረግ የሚያጠና  ጅምር በኢትዮጵያ አለ፣ ግን የገንዘብ አቅም ሰለሚጠይቅ ብዛት ያላቸውን የኮሮና ቫይረሶች ባንድ ጊዜ ማጥናት አልተቻለም፡፡ ከበርቴዎችና መንግሥት (አየር መንገድ) እዚህ ላይ ፈታ ብለው ጥናቱ ጠንከር ባለ ሁኔታ እንዲደረግ ቢያደርጉ ለሁላችንም ጥሩ ነው፡፡

ዞሮ ዞሮ ዋናው ክትባት፣ በቫይረሱ አለመያዝ ነው፡፡ የተጠየቀው ማስክ ማድረግና ስብስብን ማቆም ነው፡፡ ግን አሁን እየተሸሉ መጡ እንጂ ባለሥልጣናቱ ሲያደርጉ የከረሙት ነገር ወደኋላ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ነው፡፡ መልካም አርአያ መሆን አቅቷቸው ነበር፡፡ ክትባት ወስደውም ከሆነ፣ ሰበር ኮቪድ ሰለሚባል ነገር ቢሰሙ ጥሩ ነው፡፡ መጠኑ አነስ ይበል እንጂ ክትባት የወሰዱ ሰዎችም በቫይረሱ ሊያዙና ወደሌሎቹ ሊያቀብሉ እንደሚችሉ መረጃ አለ፡፡ መረጃ፡፡ ሲጀመር እኮ የትኛውም ክትባት መቶ ፐርሰንት የሚል ነገር የለውም፡፡ ማለቴ ከበሽታ በመስጣልም ሆነ በቫይረሱ ከመያዝ፡፡ አንድ በሉ፡፡ ሁለተኛ ክትባቶቹ፣ በጎልማሳ ሰውና በዕድሜ በገፉ ሰዎች መሀከል እኩል ምላሽ የላቸውም፡፡ ሰለዚህ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን፣ ክትባት ወሰዱም አልወሰዱም በቫይረሱ እንዳይያዙ ማድረግ የቤተሰብ አባላት ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡም ሀላፊነት ነው፡፡

ብዙ ክፉ ወሬም እየሰማን፣ የምናውቃቸው ሰዎችም ሆነ ዘመዶቻችን እየሞቱ ነው፡፡ ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡ ነገር ግን አስከ መቼ ድረስ ከዚ ቫይረስ ጋር ድብብቆሽ እንደምንጫወት ሊገባን አልቻለም፡፡ ማሰክ ሳያደርጉ በቂ ርቀት ሳይጠብቁ በቴሌቪዢን ባይታዩ ምናለበት፡፡ ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልገው አንድ መሪ ጭራሽ የማስክ አለርጂ ያለባቸው ይመስላል፡፡ ሳታውቋቸው አትቀሩም፡፡

በነገራችን ላይ፣ በኮቪድ ለታመሙ ህሙማን በኢትዮጵያ ደረጃ አይነተኛ የህክምና ርዳታ የሚሆነው አንዱና ዋናው ኦክስጅን ነው፡፡ ነገር ግን በሲሊንደር እየተሞላ የሚቀርብ ኦክስጅ በቂም አይደለም፡፡ አሁን በአሜሪካ የሚኖሩ ህንዶች እያደረጉ ያሉት፣ ገንዘብ እያዋጡ concentrator የሚባል ማሽን እየገዙ ወደ ህንድ እየጫኑ ነው፡፡ በአጋጣሚም ከአንደኛው የነሱ ሰው ጋር የመነጋገር ዕደሉ ነበረኝ፡፡ በጀምላ ከሆነ ከገበያ ዋጋ ወረድ ብሎ ይሸጣል፡፡ ችግሩ ህንዶቹ በገፍ እየገዙት ሰለሆነ በበቂ መጠን ገበያ ላይ አይገኝም፡፡ በጋራ ተሰባስብን ማድረግ የምንችለውም ነገር አንዱ ይህ ነው፡፡ እሰከዚያ ግን ለቤተሰብ ቢሆን አንዳንደ እየገዛችሁ መላክ ትችላላችሁ፡፡ ለጊዜው በደቂቃ አምስት ሊትር ኦክስጅን መስጠት የሚችለው በቂ ነው፡፡ ይህ መሣሪየ ተፈላጊ የሆነው፣ የአካባቢውን አየር ወደ ከፍተኛ መጠን ወደ ሆነ ኦክስጅን መቀየር ሰለሚችል፡፡ ኤሊትሪክ ባላበት ቦታ ሆሉ አገልግሎት መሥጠት ይችላል፡፡ በተለይም ከሆስፒታል አገግመው የወጡ ግን ኦክስጅን መውሰድ ለሚገባቸው ሰዎች ትልቅ ርዳታ ይሠጣል፡፡ ይህም በመረጃ የተደገፈ ነው፡፡

መልካም ንባብ

አካፍሉ

በቂ እንቅልፍ የሰውነት መከላከያ አቅምን ያጠነክራል

እንቅልፍና ክትባትን ምን አገናኘው? 02/14/2021 

የድረ ገፁ ጉብኝት ቁጥር  In 2020   464,511  In 2021: 100,753

እንኳን ደህና ተመለሳችሁ፡፡ ነገር ግን በርቀት 02/10/21     መንገደኞች ብቻ ሳይሆኑ የመንገደኞቹ ቤተሰቦች ሊያውቁት የሚገባ 

የአንጀት ኮቪድ የሚባል ነገር እንዳለ ያውቃሉ ወይ?
05/02/2021
ኮቪድ-19 የሳምባ በሽታ ብቻ አይደለም

ኮቪድ-19 ተራ ጉንፋን ወይም ደግሞ ኢንፍሉዌንዛ እንዳልሆነ አስመስክሯል፡፡ ችግር የፈጠረው ምንም አይነት የሳል ስሜት ሳይኖራቸው በጨጓራና በአንጀት ብቻ በሚከሰቱ የህምም ስሜትና ምልክቶች ብቻ የሚታመሙ ሰዎች መኖራቸውን ባለመንገዘብ በተጨማሪም እነዚህ ህሙማን ወደ ህክምና መገልገያ ቦታዎች ሲቀርቡ፣ የያዛችሁ ታይፎይድ ፊቨር ነው እየተባሉ ወደ ቤታቸው መመለሳቸው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገሮች፣ ህንድንም ጨምሮ የሚታይ ነገር ነው፡፡

የኮቪድ-19 በሽታን የሚያመጣው ቫይረስ ወደ ሰውነት ሲገባ የሚጠቅማበቸው ሴሎች ላይ በሚገኙ ACE-2 በተባለ ፕሮቲን አማካኝነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ፕሮቲን በላያቸው ላይ የያዙ ሴሎች ባሉበት ሁሉ ይህ ቫይረስ መዝለቁ አይቀርም፡፡ በአብዛኛው ይህ ፕሮቲን የሚታየው በመተንፈሻ አካለት ከአፍንጫ ጀምሮ እስከ ሳምባ ድረስ በሚገኙ ሴሎች ላይ በመሆኑ በዚህም ምክንያት እነዚህ የሰውነት ክፍሎች ሲጠቁ የሚታዩ የበሽታ ስሜትና ምልክቶች ይታያሉ፡፡ እነሱም፣ ትኩሳት፣ ሳል፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የመቅመስ ወይም የማሽተት ችሎታ መጥፋት ናቸው፡፡ ሆኖም ACE-2 የተባለውን ፕሮቲን በላያቸው ላይ የሚያሳዩ ሴሎች ግን ከመተንፈሻ አካላት በበለጠ በጨጓራና በአንጀት ላይ የሚገኙት ሴሎች ናቸው፡፡ አሁን ለምን የነዚህ የሰውነት ክፍሎች ሊጠቁ እንደሚችሉ ምክንያቱን የተረዳን ይመስለኛል፡፡ ACE-2 ባለበት ሁሉ ቫይረሱ ሰለሚዘልቅ ነው፡፡

ነገር ግን ምንም እንኳን በጨጓራና በትንሹ አንጀት ላይ ባሉ ሴሎች ላይ በብዛት ቢታይም፣ በትልቁ አንጀት፣ በጉበትና በምግብ መውረጃው (ኤሶፋገስ) ላይ በሚገኙ ሴሎች ላይ ግን በተለያየ ደረጃ ነው የሚታየው፡፡

ኮቪድ-19 በጨጓራና በአንጀት ህመም ሲገለጥ በብዛት የሚታዩት ስሜትና ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ተቅማጥ፣ ማቅለሽለሸና ትውኪያ፣ አይን ብጫ ቀለም ማሳየትና የሆድ ህመም ናቸው፡፡ እንግዲህ ላልጠረጠረ በሽተኛ ቀርቶ፣ ለህክምና ባለሙያም ቢሆን፣ ሰዎች ከላይ የተጠቀሱትን ስሜትና ምልክቶች ያሉባቸው ሰዎችን ሲያዩ ከኮቪድ ይልቅ ታይፎይድ ወይም ሌላ የአንጀት ህመም ነው ብለው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ አልፎ አልፎ በአይነ ምድር በኩል ደም መፍሰስ የሚታይባቸውና፣ የጨጓራ መቁሰል ወይም (አልሰር) ምልክት የሚገኝባቸው ሰዎች አሉ፡፡ የጥናቶቹ ስብስብ የሚያሳዩት፣ ምንም አይነት የመተንፈሻ አካል የበሽታ ስሜት የሌለባቸው ነገር ግ የአንጀት ኮቪድ ብቻ ያለባቸው ሰዎች እንደሚኖሩ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ከቻይና በኩል የቀረበ ጥናት የሚያሳየው ወደ ሆስፒታል ከገቡ ህሙማን አንድ አምሰተኛው የአንጀት ኮቪድ ብቻ እንደነበራቸውና በሆስፒታ ቆይታቸው ምንም አይነት የመተንፈሻ አካል ስሜት ሳያሳዩ እንደሰነበቱ ዘግቧል፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን በምርመራ ኮቪድ-19 የሚያመጣው ቫይረስ የተገኘባቸው ነበሩ፡፡ ሰለዚህ ባንድ በኩል ኮቪድ-19 እንደሚታሰበው የመተንፈሻ አካላት በሽታ ብቻ እንዳልሆነ መገንዘብ ይገባናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ ለብዙ መደናገር ምክንያትም የሚሆነው፣ ከላይ በተጠቀሰው ጥናት፣ የአንጀት ኮቪድ ከነበረባቸው ሰዎች መሀከል፣ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት በአፍና በአፍንጫ በኩል በሚደረገው ምርመራ ቫይረሱ አልተገኘባቸውም፡፡ ይህ ትልቅ ድርሻ ነው፡፡ በፐረስንት ሲገለጥ በአንጀት ኮቪድ የታመሙ ሰዎች ከ66% በላይ ቫይረሱ በምርምራ አይገኝባቸውም ማለት ነው፡፡ የዚህን ግኝት ወይም መረጃ ያላወቀ ታማሚም ሆነ አካሚ ህምመተኞቹን ታይፎይድ ነው ያለባችሁ ቢል የሚገረም አይሆንም፡፡ አደጋው እንግዲህ እነዚህ ታማሚዎች እንደሌሎቹ የኮቪድ ህሙማን በመገለያ ቦታ መቆየት ሲገባቸው ከህብረተሰቡ ጋር ይቀላቀላሉ ማለት ነው፡፡

ሌላው ጥያቄ የአንጀት ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች፣ የመተንፈሻ አካላቸው በኮቨዲ ካልተያዘ ቫይረሱን ማስተላለፍ ይችላሉ ወይ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በጎሽ ድረ ገፅ እንደተገለፀው፣ የኮቪድ-19 ቫይረስ በአይነ ምድር ንክኪ አማካኝነት ሊታላለፍ እንደሚችል ነው፡፡ በተደረጉ ክትትሎች የአንጀት ኮቪድ ብቻ ከነበራቸው ህሙማን ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች ቆየት ብለው የኮቨድ-19 በሽታ እንደተያዙ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል የጥናቶች ስብስብ የሚያስረዳን ነገር ቢኖር፣ በኮቪድ-19 የተያዙ ህሙማን፣ የእንጀትም ሆነ በሌላ መንገድ የተያዙትን ጨምሮ፣ ወደ 43% የሚሆኑት በአይነ ምድራቸው ላይ ቫይረሱ እንደሚገኝ ነው፡፡ የሚያሳስበው ደግሞ በአይነ ምድር በኩል የሚገኘው ቫይረሰ የበሽታ ምልክት ወይም ስሜት ከተነሳበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰባ ቀናት ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ነው፡፡ ማለትም በሌላ ጥናት እንደተመለከትኩት በመተንፈሻ አካላቸው በሚደረገው ምርመራ ቫይረሱ ነፃ ነው እየተባለ በአይነ ምድር በኩል ግን ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች አሉ፡፡ ዋናው ሙግት ያለው በአይነ ምድር አማካኝነት ምን ያህል ከሰው ወደ ሰው ይተላፋል ነው፡፡

ሌላው ችግር የሚነሳው ደግሞ፣ የአንጀት ኮቪድ ብቻ የያዛቸው ሰዎች፣ በኮቪድ አልተያዝንም ሰለሚሉ ወደ ህክምና ቦታዎች ቶሎ አይቀርቡም፡፡ ቢቀርቡም እንኳን የያዛቸው ኮቪድ ነው ብሎ ለመጠርጠር ጊዜም ይወስዳል በተጨማሪም በአፍና በአፍንጫ በኩል ለቫይረሱ በሚደረገው ምርመራ ቫይረሱ ሰለማይገኝ፣ ህክምናው ሊጓተትና ወይም ሌላ የማይገናኝ ህክምና ሊሠጣቸው ይችላል፡፡ እነዚህ ህሙማን በአብዛኛው ጊዜ ታይፎይድ አለባችሁ እንደሚባሉ ከሰዎች ጋር በተደረገ ቃል ልውውጥ መረዳት ተችሏል፡፡

ጥናቶች የሚያስረዱት የአንጀት ኮቪድ በተወሰኑ ሰዎች ብቻና ደግሞም በተወሰነ አካባቢ ብቻ ሊታይ እንደሚችል ነው፡፡ ለዚህ የተለያዬ የመገለጥ ሁኔታ ሚስጥሩ ገና አልታወቀም፡፡ እንደ ቫይረሱ ሥርጭት፣ የአንጀት ኮቪድ ብቻ ይዟቸው ያገገሙ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ርግጠኛ ነኝ፡፡ በሥራ መስክም የአንጀት ኮቪድ ብቻ ተይዘው ሆስፒታል ድረስ ሄደው የኮቪድ ምርመራው ቫይረሱ አልተገኘባቸውም ተብለው የተመለሱ ህሙማን በቁጥር አነስ ያሉ ቢሆንም ራሴ የተከታተልኳቸው ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ህሙማን ግን ለኮቪድ 19 መጋለጣቸውን ርግጠኛ ሰለነበርን፣ በቤትም ሆነ በሆስፒታል እንደ ኮቪድ በሽተኛ ነበር የታከሙት፡፡ ወደ ኋላ ለቫይረሱ መጋለጣቸው ለማረጋገጥ በተደረገ የደም ምርመራ በርግጥም ተይዘው እንደነበረ ማረጋገጥ ችለናል፡፡ በኛ በኩል ጥያቄው የነበረው፣ ምን ያህል ሰዎች፣ የእንጀት ኮቪድ ብቻ ሊያዙ እንደሚችሉ ማወቁ ነወ፡፡

ዋናው ምክር፣ የኮቪድ በሽታ ሥርጭት ከፍ ባሉባቸው ቦታዎች፣ የአንጀት ኮቪድ ብቻ ሊይዛቸው የሚችሉ ሰዎች መኖራቸውን ህሙማኑም ሆነ አካሚዎቹ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ሰለዚህ በቂ ጥርጣሬ ካለ፣ ለነዚህ ህሙማን ህክምና ሲሠጥ በቂ የመከላከል ፕሮቶኮል ባለበት ሁኔታ እንዲሆንና፣ ወደ ቤትም የሚመለሱ ከሆነ፣ በሽታው ረገብ እስከሚል ወይም ለአስር እሰከ አስራ አራት ቀናት ገለል እንዲሉ፣ የራሳቸውን የንፅህና መገልገያዎች ለብቻ እንዲጠቀሙ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እዚህ ላይ እንግዲህ እጅን ቶሎ ቶሎ መታጠብ አስፈላጊነቱን መገንዘብም ይኖረብናል፡፡ በአብዛኛው ጊዜ በተቅማጥና በትውከት በኩል አደጋ የሚከሰተው የሰውነት ድርቀት በማምጣት ስለሆነ፣ ከሰውነት የወጣውን ፈሳሽ መተካት አይነተኛ የህክምና ዘዴ ነው፡፡

የዚህ ፅሁፍ መረጃዎች ስፋትና ብዛት ስላላቸው በዚህ አልተጠቀሱም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ አርፈተ ነገርና እንቀፅ በመረጃዎች የተደገፈ መሆኑን እንባቢያን እንዲረዱ አስገነዝባለሁ፡

በኮቪድ 19  ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተዘገበው በላይ ዕጥፍ ነው ተባለ

ሰበር ኮቪድ ደግሞ ምን ይሆን?

 ከተከሰተ አንድ አመት ያሳለፈው ወረርሽኝ መለስ ሄደት እያለ አንዳንድ ቦታም አራተኛ ዙር ድረስ እየተመላለሰ መክረሙ ለሁላችንም ግልፅ ነው፡፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን መንግሥታቱ በየሀገራቸው በበሽታው የተያዙ፣ ያገገሙ በሎም የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ ሁላችንም እንደምንከታተለው ይህ አሃዝ በየቀኑ እየታደስ በመገናኛ ብዘሁን ይተላለፋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ በሚኖሩ ወገኖች በኩል፣ በኮቪድ የተያዘ፣ በኮቪድ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ ሰው የማያውቅ የለም ብሎ መናገር ያስደፍራል፡፡

አሰከዛሬው ዕለት ጆንስ ሆፕኪንስ ዩነቨርስቲ በየቀኑ በሚያሳየው ግራፍ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3.2 ሚሊዮን ነው፡፡ ቀዳሚነቱን የያዘችው አሜሪካም 580,000 አስመዝግባለች፡፡ ከአሜሪካ ቀጥሎ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጎዱት አገራት ደግም የደቡብ አሜሪካና የካሪቢያን ደሴቶች ናቸው አሁን በህንድ የሚታየውን ሳይጨምር፡፡ ታዲያ ተንታኞቹ የሚሉት፣ በኮቪድ-19 ምከንያት የሞተው ሰው ቁጥር 6.9 ሚሊዮን ነው፡፡ ያ ማለት በአሃዝ በአደባባይ ከሚታወቀው ዕጥፍ መሆኑ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ የህክምና ተቋማት በደረሰባቸው ቸግር ምከንያት በህከምና አገልግሎት ማነስ ወይም አለመኖር ምክንያ የሞቱ ህሙማንን ሳይጨምር ነው፡፡

ይህን ቁጠር ያስቀመጠው Institute of Health Metrics and Evaluation (IHME) የተባለ በአሜሪካ University of Washington School of Medicine የሚገኝ ቡድን ነው፡፡

ቡድን ለትንነተና የተጠቀመበትን ዘዴ መመልከቱም ይበጃል፡፡ ያም ሆኖ መንግሥታቱ የሚዘግቡት የሟች ቁጥር ከዐውነታው ያነሰ መሆኑን ሁላችንም ግምቱ አለን፡፡ በኮቪድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሪፖርት ውስጥ የማይገባበት አንደኛው ምክንያት፣ አገሮቹ ሪፖርት የሚየደርጉት የሟች ቁጥረ በበሽታ ተይዘው በሆስፒታል ውስጥ ሲሞቱ በኮቪድ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎችን ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ብዛት ባላቸው ቦታዎች፣ ደካማ የሆነ የጤና ሪፖርት አሰራር ባለመኖሩ በተጨማሪም ወደ ሆሰፒታል ገብቶ ህክምና ለማግኘት ብቃት አለመኖሩ የሟቾችን ቁጥር በትክክል መግለፅ ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡

እንደ IHME ግኝት፣ በሪፖርት ያልተካተቱ የሟቾች ቁጥር በብዛት የታየው ወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ የተሠራጨባቸው አገሮች ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ አገሮች በንፅፅር መጠነኛ የወረርሽኝ ሁኔታ የታየባቸው ቢሆንም ሪፖረት ውስጥ ያልተካተተ ግን ከሌላ ጊዜ በላይ የሟቾች ቁጥር ከፍ ብሎ ማግኘታቸው ይታወቃል፡፡ የሟቾችን ትክከለኛ ቁጥር በብዙ ረገድ ኢኮኖሚውን ጨምሮ ዕቅድ ማውጣት ላይ ይረዳል ይላሉ ሙያተኞቹ፡፡

IHME የሚሉት ትንተናው መሠረት ያደረገው፣ ከ1990 ጀምሮ በአለም ላይ በበሽታ ምክንያት በሰዎች ላይ የሚደረሰውን ጉዳት በመለካት ነው፡፡ በዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ በበሽታ ምከንያት በሰው ሕይወት ላይ የደረሰውን አደጋም በመለካት ነው፡፡

ቡድኑ ያደረገው በኮቪድ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመገመት፣ በየአመቱ በማንኛውም ምክንያት በየአመቱ ከወረርሽኙ በፊት የመገመተውን ወይም ከሚጠበቀው የሟቾች ቁጥር ጋር በማነፃፀር ነው፡፡ ከሚጠበቀው በላይ የታየው የሟቾች ቁጥር ትርፍ ሞት (Excess death) ወይም ያልተጠበቀ የሞት ቁጥር ነው፡፡ ይህን ሲያሰሉ ትርፍ ሆኖ ወይም ከተጠበቀው በላይ ከተገኘው የሟቾች ቁጥር መሀል በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ በወረርሽኙ ጊዜ አገልግሎት በማጣት በሌላ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ቀንሰው ነው፡፡ በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች እምብዛም ሰለማይንቀንቀሱ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱሰ ሰዎች ቁጥር መቀነሱንም ታሳቢ አድርገው ነው፡፡ ይህ ሁሉ ስሌት ከተደረገ በኃላ ቀሪው ሞት በኮቪድ 19 ምክንያት ነው የሚሉት፡፡ እንግዲህ ከዛ ውስጥ ምን ያህሉ ነው በሪፖርት የቀረበው፡፡ በሪፖርት ካልቀረበው ጋር ሲደመር የሟቾች ቁጥር ከሚታወቀው በላይ ከፍ እንደሚል ነው፡፡

ባደረጉት ስሌት የአንዳንድ ሀገሮችን ትክከለኛ የሟቾች ቁጥር ያሰቀመጡበትን ዘገባ ላከፍላችሁ፡፡

ለምሳሌ የአሜሪካን ብንወሰድ፣ በአደባባይ የሚታወቀው የሟቾች ቁጥር 574,043 ሲሆን በነሱ ስሌት ግን በኮቪድ ምክንያት የሞተው ጠቅላላ ቁጥር 905,289 ነው የሚሉት፡፡ ይህ ቁጥር ስሌት ባደረጉበት ቀን የነበረው ነው አንጂ ከስሌቶ በኋላ ቁጥሩ በየቀኑ እንደሚጨምር ይታወቃል፡፡ ህንድ ሪፖርት ያደረገችው 221 181 ሲሆን በነሱ ስሌት 654,395 ነው፡፡ ብራዚል 408 680 ሲሆን በስሌቱ 595,903 ነው፡፡ ሜክሲኮ ደግሞ 217,694 ሪፖርት ቢያደርጉም በስሌቱ 617,127 ነው፡፡ ሩሲያ 109,334 ሲሆን በስሌት ደግሞ 593,610 ነው ይላሉ፡፡ ወደ አፍሪቃ ልውሰዳችሁ ግብፅ ሪፖርት ያደረገችው 13,529 ነው ግን ግምቱ 170,041 ይላሉ፡፡ ደቡብ አፍሪቃ ደግሞ 54,390 ሪፖርት ብታደርግም ጠቅላላ የሟች ቁጥር 160,452 ነው፡፡ የብዙ ሀገራት ቁጥሮች ተዘርዝረዋል፣ የጠቀስኳቸው ግን ሪፖረት ያደረጉት ቁጥር ከጠቅላለው በግማሽ ያነሰ የሚመስሉትን ነው፡፡ ጃፓንም ቢሆን ሪፖርት ያደረገችው 10 390 ሲሆን እነሱ የሚሉት 108 320 ሞቶባታል ነው፡፡ እንደሚታወቀው የሟች ቁጥር የሚመመዘገብ ነገር ነው፡፡ በምን ምክንያት ነው የሞቱት የሚለው ነው ስሌት ውስጥ የሚገባው፡፡ የሚያሳስበውና የሚያሰፈራው ሊደርስ ይቻላል ብለው በሚያሰሉት (ሞዴሊንግ) በመስከረም በአለም ላይ የጠቅላላ ሟቾች ቁጥር 9.4 ሚሊዮን ይሆናል ነው የሚሉት፡፡ የምታስታውሱ ካላችሁ ከዚህ ቀደም ወረርሽኙ እንደጀመረ የተለያዩ ቡድኖች በኮቪድ ምክንያት ሊሞት የሚችለውን ቁጥር ግምት እየገለፁ እንደነበር ነው፡፡ የታየ ነገር ቢኖር የሞት ቁጥር እነሱ ከገመቱት በላይ ነው የሆነው፡፡ አሁንም ከገመቱት በላይ እንዳይሆን ፈጣሪ ይርዳን፡፡ ግን ሀላፊነቱ መልሶ የኛ ነው፡፡ መከላከያ ዘዴዎችን ተግባራዊ አለማድረግ ጣጣውን እየጨመረብን ነው፡፡

የኢትዮጵያን ግምት አቅርብ ከማለታችሁ በፊት፣ በ IHME ሪፖርት አሁን ባለው ከቀጠል በመስከረም 2021 አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 22 293 ይሆናል ነው የሚሉት፡፡ ይህ ቁጥር በራሱ ብዙ ቢሆንም፣ እንደ ሁኔታው ከሆነ ያነሰ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ጠንከር ብሎ የተጀመረውን የመከላክል ተገግባር ሁሉም ቢከተልና የፖለቲካ መሪዎችም ሆነ ታወቂ ሰዎች ማስክ በማድረግና የአካል ርቀት በመጠበቅ አርአያ ቢሆኑ፣ የእምነት ተቋማትም ተከታዮቻቸውን ለማዳን የመከላከያ ዘዴዎችን ቢመክሩ፣ ሁኔታው ሊቀለበስ ይችላል፡፡ አዚህ ላይ ክትባት ወስጃለሁና አይዘኝም ብሎ መዝናናት አደገኛ ነገር መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ በመጀመሪያ የወሰዱት የክትባት አይነት በቫይረሱ ከመያዝ ማስጣል የሚችለው በምን ያህል ፐርስንት አንደሆነ ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ ከዛም አልፎ በቫይረሱ እንኳን ቢያዝ ምን ያህል ሰው ከከፋ በሽታ ይድናል የሚለውን አሃዝ ወይም ፐርስንት ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ አዚህ አሜሪካ እሰካሁንደ ድረስ በሰበር ኮቪድ፣ ማለትም ክትባቱን ወሰድው በቫይረሱ ከተያዙ መሀል ወደ ሰባ ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡ አንድ የሚያሳዝን ዜና ደግሞ፣ የተላላፊ በሽታዎች ስፔሺያሊስት የሆነ፣ ክትባቱን የወሰደ ሀኪም ወደ ህንዳዊ ሰለነበር ህንድ አገር ሄዶ ለርዳታ ሲሰራ እዛው በኮቪድ ተይዞ ሕይወቱ አልፏል፡፡ በሰበር ኮቪድ ተይዘው የሞቱት ሰዎቸ፣ ከድሮውመ ቢሆን በኮቪድ ቢያዙ አደጋ የሚደርስባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ማለትም በዕደሜ የገፉና ተደራቢ በሽታ ያለባቸው ሰዎች፡፡ ሌላው ችግር እነዚህ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ክትባት ቢወሰዱም እንደ ጎልማሳው ወይም ወጣቱ ጠንከር ያለ የመከላከያ አቀም እንደማይፈጥሩ ይታወቃል፡፡ ሰለዚህ ክትባት ቢወሰድም ለነዚህ ሰዎች ሲባል፣ ጥንቃቄው እንዲቀጥል አጠይቃለሁ፡፡ እኛም ራሳችን ክትባቱን ብንወሰድም ገና አብዛኛው ሰው ክትባት ወስዶ ሥርጭት ቀነሶ ነፃ እስከምወጣ ደርስ መዘናጋት አያስፈልግም፡፡ ከራስ በተጨማሪ፣ ክትባት የሚወሰድብት ሌላው ሰብዓዊ ምክንያት ሥርጭቱን ለመቀነስ ነው፡፡

የአሜሪካው ሲዲሲ ክትባት ለወሰዱ ሰዎች ባወጣው መመሪያ፣ ያለ ማስክ መቀላቀል የሚቻለው ክትባቱን ከወሰዱ ሰዎች ጋር ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ጥንቃቄው ጥሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የምናየው ማስክ ያደረገና ያላደረገ ጎን ለጎን ተቀምጦ ነው፡፡ ክትባት በመውሰድ ከቤት ውጭ በሚደረጉ ግንኙነቶች ምክሩ ለቀቅ ቢልም በቤት ውስጥና በአዳራሾች ግን ጥብቅ ምክሩ እንደቀጠለ ነው፡’¨<

በዚህ በኮቪድ ከመጣ ሁሉም ሰው መካሪና አስተማሪ መሆን አለበት፡፡ አናምንምና ምንም ነገር አናደርግም የሚሉ ሰዎች ራሳቸውን ገለል አድርገው እንደፈለጉ ይሁኑ ግን ከአንዱ ወደ አንዱ ቫይረሱን ባያቀባብሉ ጥሩ ነው፡፡ ሌሎችም ቢሆን በሚገድል ነገር ይሉኝታው ቢቀር ጥሩ ነው፡፡ ያልፋል እናሳልፈው፡፡ አሜን፡፡raph here.