ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ
አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ

Community health 

education in Amharic 

ማስክዎን የሚያወልቁባቸው ቦታዎች ያጋልጡዎት ይሆን? 4/18/20

 ሀሉም ሰው ማሰክ እንዲያደርግ ሲመከር፣ ዋናው ምክንያት፣ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚተነፍሱበት፣ በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ጊዜ፣ ከትንፈሻቸው የሚወጡትን ቫይረስ የተሸከሙ ጠብታዎችን ለመገደብ ነው፡፡ አሁን እንግዳ የመሰለው፣ ግን ከመጀመሪያው የታወቀው ነገር፣ በቫይረሱ ተይዘው የበሽታ ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ለቫይረሱ መተላለፍ ብቻ ሳይሆን በፍጥነት ለመሠራጨት ምክንያትም መሆናቸው ነው፡፡

ጥሩ ምክር ነው፣ እርስዎም ምክሩን ሰምተው ማስክ አድርገው ሲወጡ ለሌሎቹም ምሳሌ ሰለሚሆኑ፣ ማሰብ ያለብዎት፣ ቫይረሱ ባይኖርብዎት አንኳን፣ ሁሉም ሰው እንደስዎ ማሰክ ካደረገ፣ ካለባቸው ሰዎች የሚወጣው ቫይረስ ሰለሚገደብ በምሳሌ ያደረጉት ነገር፣ አስዎንም ሆነ ሌሎችን ከመያዝ እንዲከላከል የረዱ መሆኖዎን በማሰብ በሚችሉት መንገድ ሥርጭቱን ለመግታት ከሚታገሉት ወገኖች ራስዎን ይመድቡ፡፡

አሁን፣ ሁላችንም ለተወሰነ ሰከንዶች ቆም ብለን ብናስብና ብንጠይቅ፣ የጤና ባለሙያ ሆኑ ሌላም፣ ማስክዎ  ከፊትዎ የሚያውልቁባቸው ቦታዎችን ይቁጠሩ፡፡

አንደኛው በግልፅ ለብቻዎ ሲሆኑ፣ በመኖሪያ ቤትዎ ወይም በመኪናዎ ውስጥም ሊሆን ይችላሉ

ሁለተኛ፣ ግልፅ የሚሆነው፣ ምግብ ወይም መጠጥ በሚወስዱበት ጊዜ ነው፡፡ በተለይም ምግብ ሊበሉ ሲሉ ነው፡፡ ጥያቄው ደግሞ የት ነው የሚበሉት ነው፡፡ በሥራ ቦታ ከሆነ የት ክፍል?

ሶሰተኛ፤ ብዙ ሰዎች ወደ መፀዳጃ ክፍሎች ሲገቡ፣ ብዙ ጊዜ የሚያደርጉት ነገር፣ ከአጅ መታጠብ ጋር አፋቸውን ፊታውን መጥረግ አክታ ወይም ምራቅ መትፋትን ይጨምራል፡፡ በዚህኛውም ላይ፣ ጥያቄው፣ መፃዳጃ ቤቱ የት ነው የሚለው ነው፡፡

ከዚህ ቀደም፣ በዚህ በጎሽ ገፅ እንደተገለፀው የሳርስ ኮሮና ቫይረስ-2፣ በአየርና በዕቃዎች ላይ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል ለሚለው ጥያቄ፣ አጥኝዎች ያካፈሉን ነገር አለ፡፡ ከነሱ አንደኛው፣ ቫይረሱ በተዘጋ ክፍል ወይም አየር እንደልብ በማይዛወርበት ክፍሎች፣ ቫይረሱ ለሶስት ሰአታት ያህል ተንሳፎ ሊቆይ እንደሚቸል ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ በየጊዜው የሚተገበር አዲስ ያልሆነ ነገር፣ በህክምና ተቋሞች ውስጥ፣ እንደዚህ አይነት ተላላፊ በሽታዎች ያላባቸው ወይም የሚጠረጠሩ ሰዎች የሚቆዩበት ክፍል፣ በአንግሊዝኛው Isolation room ተብለው የሚጠሩ፣ በክፍሉ የሚገኘው አየር በዛው በክፍሉ ብቻ እየተዛወረ እንዳይቆይ፣ አየሩን ወደ ውድ መሳብ የሚችሉ መሳሪያዎች የተጠመዱበት ክፍል ነው፡፡ አሁን አንደ የዚህ አይነት ነገር የሌለው ክፍል፣ ደንገት አፍና አፍንጫውን ባልሸፈነ ህሙም ሳልና ንጥሻ ተጋለጠ ቢባል፣ ክፍሉን ለሌላ በሽተኛ ከመጠቀም በፈት፣ ክፍሉ እንደ አየሩ ዝውውር፣ ለአንድ ሰአት ግፋ ሲልም ለሶሰት ወይም አራት ሰአታት ተዘግቶ ይቆያል፣ ለማፅዳት የሚገቡ ሠራተኞች አንኳን ሙሉ መከላከያ ልብስ አድርገው ነው የሚገቡት፡፡ እንግዲህ ወደ ሆስፒታል የዘለቃችሁ ሰዎች፣ የምርመራ ክፍሎችን ስፋት ማስታወስ ትችላላችሁ፡፡ ይህ የሚሆነው፣ ከጥዋቱም ቢሆን በአየር ላይ ተንሳፎ የሚቆይ ቫይረስ መኖሩ ስለሚታወቅ ነው፡፡

ወደ ማስክ ማውለቂያ ቦታዎች ስንመለስ፣ ሥንሠራ ውለን ግን ለምሳ ሰአት ማስኩን ስናወልቅ፣ በተለይ በሥራ ቦታዎች፣ ጠበብ ያሉ የምግብ ቦታዎችን ከሌሎች የሥራ ባልደሮቦች ጋር በመጋራት ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ሰሜት አልባ የሆነ በቫይረሱ የተያዘ ሠራተኛ ቢኖር፣ መጋለጥ ይመጣል፡፡ የቻይና ሆስፒታሎች ይህንን የተገነዘቡት ቀድም ብለው ሰለነበር፣ የጤና ባለሙያ ብቻውን በአንድ ጠረጴዛ እንዲበላ እንጂ ከባልደረባ ጋር እንዳይቀመጥ ይከልክላሉ የሚል መረጃ አይቻለሁ፡፡ ለዚህ ነው፣ ከዚህ ቀደም ምክር ስሰጥ፣ ከቻላችሁ ከነማስካችሁ ወጣ በሉና፣ መኪና ያላችሁ በመኪናችህ ውስጥ ብቻችሁን፣ አለዚያመ ከሌች ሰዎች ራቅ ባለ ሰፋ ያለ ቦታ መመገብ ይመረጣል፡፡

ወደ መፀዳጃ ቤት እንመለስ፣ በአብዛኛው በአንድ ህንፃ ወስጥ ጠበብ ያሉ ክፍሎች መፀዳጃ ቤቶች ናቸው፡፡ ፅሁፌን ሳልጨረስ፣ ነገሩን የደመደማችሁ እንደምትኖሩ ይገባኛል፡፡ መፀዳጃ ቤቶች ደግሞ ሁሉም ሰው ነው የሚገለገልባቸው፡፡ በነዚህ ክፍል ጉሮሮውን የሚያጠራ የሚያስነጥስ ሰውም ይኖራል፡፡ የተያዘም ያልተያዘም፡፡ ወደኋላ መለስ ብላችሁ ካያችሁ፣ ቫይረሱ በአየር ላይ ምን ያህል ሰአት ሊቆይ እንደሚችል፣ በህክምናው አለም ተብክሏል የተባለን ክፍል መልሶ ከመጠቀም በፊት የሚወሰደውን ርምጃ ካስተዋላችሁ፣ መፀዳጃ ቤቶች አደገኛ ሰልፍ ውስጥ ይገባሉ፡፡ በጋራ የምንጠቅምባቸውን መፀዳጃ ቤቶች ማለቴ ነው፡፡

ሰለዚህ፣ በነዚህ ቦታዎች፣ ማስክዎን ከማውለቅ ይቆጠቡ፡፡ ሌላው እዚህ ላይ መጨመር የምፈልገው፣ የማስኩ የፊት ለፊት በኩል፣ የተጋለጠ በመሆኑ፣ በእጅዎ ከመነካካት ይቆጠቡ፣ ሲያወልቁም በጥንቃቄ መሆን አለበት፡፡ዋናው ምክር ደግሞ፣ ሁላችንም ቢሆን ቫይረሱ ኖረንም አልኖረንም የምናደርገው ጥንቃቄ ቫይረሱ እንዳለበት እንዲሆን ነው፡፡ አንድ ላይ ተጋግዘን መስራት መቻልና አለመቻላችን የሚፈትን ነገር ነው የመጣብን፡፡

መልካም ንባብ

አካፍሉ

ጥብቅ ማሳሰቢያ

መንግሥት፣ ዛንታክ የሚባል መድሐኒት ከደጃፌ አይብቀል እያለ ነው!

ከዚህ ቀደም፣ ራኒቲዲን ስለተባለ መድሐኒት፣ ከካንሰር ኬሚካሎች ጋር መነካካት በተመለከት በጎሽ ድረ ገፅ በማቅረብ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክረናል፡፡ ይህ ራኒቲዲን የተባለው መድሐኒት ለጨጓራ ህመም የሚሠጥ ነው፡፡ የተለያዩ አምራቾች ሰለሚያወጡት በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ ከዚህ በፊት የተወሰኑ ምርቶች ላይ ነበር ያተኮረው፡፡ አሁን ግን፣ በዚህ በግርግር መሀል፣ የአሜሪካው የምግብና የመድሐኒት አስተዳደር፣ በቅርቡ ባወጣው ትዛዝ፣ ሁሉም የዚህ መድሐኒት ዘሮች ለህዝብ አገልግሎት እንዳይቀርቡ፣ ከመደርደሪያ እንዲነሱ ይገልፃል፡፡

ያ ማለት ደግሞ የዚህ መድሐኒት ዘር በጠቅላላ አግልገሎት ላይ እንዳይውል ነው፡፡ አንደ አስተዳደሩ አገላለጥ፣ የህ መድሐኒት የተነካካ በመሆኑ፣ በመደርደሪያ ላይ ሲሰነበትም፣ ምን ችግር እንደሚያስከትል ስለማይታወቅ፣ ጥንቃቄውን የመረጡ ይመስላል፡

አንባቢ ደግሞ፣ መንግሥት ጨክኖ አንድን ምርት አይኑን እንዳላየው ካለ፣ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ሰለዚህ፣ ካሁን በኋላ ከፋርማሲ የማታገኙት ቢሆንም፣ በየቤታችሁ ያለ ካለ ማስወገድ አስፈላጊ ነው፡፡ ላልሰማ አሰሙ፡፡ ይህ መድሐኒት በሌላ ስሙ ዛንታክ ይባላል፡፡ 


ከካንሰር ኬሚካሎች የተነካካው መድሐኒት፣ ዛንታክ Zantac ይባላል ዋናው ኮምፓውንዱ ራኒቲዲን Ranitidine ነው፡፡