ኢቦላ     በጣም ጥሩ ውጤት የሚያሳይ ክትባት መገኝት

ስለ ኢባላ አስከፊነት ስንሰማ የከረምን መሆኑን አናስታውሳለን፡፡ የዚህን በሽታ ተላለፊነትና በዚህ በሽታም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከዚያም በተጨማሪ በምዕራባዊ የአፍሪካ ክፍል የሚገኙ በተለይም ሶስት ሀገሮች ብዙ ችግር ላይ እንደወደቁ ማሰታወስ ተገቢ ነው፡፡
አሁን ደግሞ ጥሩ ውጤት የታየበት የክትባት ምርምር ደረጃን ለማካፈል እንወዳለን፡፡ የተላላፊ በሽታዎች በሚባል መፅሔት ዘገባ መሠረት ምርምር ወይም ጥናት ጥናቱ ከማለቁ በፊት በተደረገው ትንተና መሠረት አራት ሺ በላይ ሰዎች ላይ ጊኒ በሚባል አገር ውስጥ የተሠጠው ይህ የምርምር ክትባት ሰዎችን በመቶ ፐርሰንተ ከኢቦላ መከላከል መቻሉን ያሳያል፡፡ በዚህ ጥሩ ውጤት ምክንያት ክትባቱ ለሁሉም ጥናቱ ውስጥ ላሉ ሰዎች በተመሳሳይ ጊዜ አንዲሠጥ ተወስኗል፡፡
ስለ ጥናቱ ለማብራረት ይህ rVSV-ZOBOV የሚባል ክትባት ከሌላ ቫይረስ ክፍል በመነሳት በካናዳ የተሠራ ሲሆን ለሌሎች ካምፓኒዎች በፈቃድ የተሠጠ ነው፡፡ ለዚህ ክትባት ጥናት መቅረብ ከጊኒ መንግስት ጀምሮ ሌሎችም የአሜሪካንም መንግሥት ጭምር አስተዋፅኦ ያደረጉበት ነገር ነው፡፡
የክትባቱ ጥናት የተጀመረው በማርች 3 ሲሆን ለኢቦላ የተጋለጡ ሰዎች በተለይም በግልፅ የኢቦላ በሽታ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች እኩል በሆነ ቁጥር ወይም ብዛት ከሁለት በኩል ተከፍለው ግማሾቹ ክትባቱ ወዲያውኑ እንዲሠጣቸው ግማሾቹ ደግሞ ከ21 ቀናት በሁዋላ በመዘግየት ክትባት እንዲሠጣቸው ተደረገ፡፡ አንዚህ ቁጥራቸው 4123 የሚሆኑ ሰዎች ከ100 የተረጋገጠ ኢቦላ በሽታ የተገኘባቸው ሰዎች ጋር  የተጋለጡ ሰዎች ናቸው፡፡
ክትባቱ ከተሠጠ ከአስር ቀናት በሁዋላ በተደረገው ግምገማ ክትባቱን ወዲያውኑ የወሰዱ ወገኖች በኩል ማንም ሰው በኢቦላ ያልተያዘ ሲሆን በተቃራኒው ግን ክትባቱን ዘግይተው የወሰዱ ሰዎች መሀከል 16 ሰዎቸ የተረጋገጠ ኢቦላ ተይዘዋል፡፡ በሳይንሳዊ ስሌት እንደጥናቱ ተመራማሪዎች ክትባቱ 100 ፐረስንት ውጤታማ ነው፡፡ በዚህ ውጤት ምክንያት ሌሎች ጥናቶች ላይ አንደሚደረገው ሁሉ ውጤቱ በጣም ጥሩ ስለሆነ ምርምሩ ይቆምና ክትባቱ ለሁሉም ሰዎች ወዲያውኑ እንዲሠጥ ይደረጋል፡፡ ሆኖም በሌላ መልክ ጥናቱ ይቀጥላል ይህም እድሜያቸው ከ13- 17 ክልል ያሉ ልጆችን ክትባቱን መሥጠት ወደፊትም ልጆች እድሜያቸው ከ6-12 የሆነቱን እንደሚጨምር ነው፡፡ ከዚህ በሁዋላ ደግሞ የጥናቱን ውጤት መከታተል ነው፡፡
ዋናው አላማ ከዚህ በፊት በፈንጣጣ ክትባት ተለምዶ መሠረት በሽተኞች ባሉባቸው አካባቢ ዙሪያውን የሚገኙ ሰዎችን በመከተብ በሽታው ወደ ሌላ ቦታ አንዳይዛመት ማድረግ ነው፡፡ ይህ ዘዴ መከላከያ ቀለበት ይባላል፡፡ በነገራችን ላይ በክትባት ብቻ ጠፋ ተብሎ የሚታወቅ በሽታ ቢኖር ፈንጣጣ (Small Pox) መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡