መፅሐፉ የሚገኝባቸው ቦታዎች

 1. በዋሽንግተን ዲሲ፣ እንጦጦ ገበያ
 2. በሜሪላንደ፣ ሲልቨር ስፐሪንግ፣ ኤርታ አሌ ምግብ ቤት
 3. በቨርጂኒያ፣ በአርሊንግተን፣ ዳማ ምግብ ቤት
 4. በቨርጂኒያ፣ አለክሳንድሪያ፣ ህብር ምግብ ቤት
 5. ​በናዝሬት ባልትና በቨርጂኒያና በሜሪላንድ ሱቆቻቸው
 6. በኔብራስካ ኦማሃ አድራሻ  3301 California st, Omaha  Nebraska 68131

ጥር 6 (January 14th)

አፄ ቴዎድሮሰ የተወለዱበት ቀን

መቅደላ የቴዎድሮሰ ዕጣ 

ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ በድፍን ኢትዮጵያ ተወዳጅና ገናና ሰለነበሩት ንጉሥ ስለ አፄ ቴዎድሮስና ሰለ መቅደላ ዘመቻና ፍፃሜ ለአንባብያን አቅርበዋል፡፡
አሜሪካዊ ጋዜጠኛ በአካል መቅደላ ተገኝቶ ያየውንና የዘገበውን የሚገልፅ ፅሁፍ ትርጉም ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ብዙም የማናውቃቸውን ነገሮች አካቶ፣ የምናውቃቸወን ደግሞ በጥልቀት ይገልፃል፡፡
ስለ ንጉሡ አሟሟት ግልፅና በሆነና በማያሻማ ሁኔታ ይገልጣል፡፡
ዶ/ር ገበየሁ ተፊሪ፣ ከትርጉሙ በተጨማሪ ከአስራ አምስት በላይ የሚሆኑ ፅሁፎችን በመመርመር፣ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ባህሪ ቁመናና ጥንካሬ መረጃዎችን በግርጌ ማስታወሻ  መልክ ለአንባቢ አቅርበዋል፡፡
ብዙ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ባህሪ የማናውቃቸው ሁኔታዎችን ያጋራል፡፡ በተጨማሪም ከ30 በላይ የሆኑ ምስሎችን በመጨመር የመቅደላ ዘመቻ ምን ይምስል እንደነበር ያጋራል፡፡
በእውን አፄ ቴዎድሮስ የሼክሰፔርን ሥራዎች ያውቁ ነበር? በርግጥም ያውቁ ነበር፡፡ ሌሎች ብዛት ያላቸው የንጉሡን ሃሳብና ጥልቀት የሚመዝኑ ወይም የሚገልፁ መረጃዎች ተካተውበታል፡፡
ይህ ፅሁፍ ስለ አፄ ቴዎድሮስ አጠቃላይና ጥልቅ ግንዛቤ ከመስጠቱም በላይ፣ የመቅደላን ሁኔታ በስዕላዊ መንገድ ስለሚገልፅ አንባቢ ራሱን መቅደላ አምባ ላይ ቢያሰቀምጥና ሁኔታውን ቢከታተል የሚገርም አይሆንም፡፡

ከአንባቢዎች የተሠጡ አስተያየቶች

 1. ይህን መፅሐፍ እሰከማነብ ድረስ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ብዙ ያነበብኩ ይመስለኝ ነበር
 2. በጣም ብዙ አዲስ ነገር ነው የተማርኩት
 3. ይህ መሆኑን አላወቅሁም ነበር
 4. የተዋጣለት ትርጉም፣ ነገር ግን በግርጌ ማስታወሻ የተፃፉት ሥራዎች ሌላ መፅሐፍ ይወጣው ነበር፡፡ ተርጓሚው ራሱን ችሎ ሌላ መፃፍ ይችል ነበር፡፡
 5. የቋራው አንበሳ አውሮፓውያን እንደሚያስቡት ተራ ሰው ወይም ተራ መሪ አልነበረም

በመፅሐፉ ምረቃ በፀሀፊው በዶክተር ገበየሁ ተፈሪ የተሠጠ መግለጫ  ቪዲዮ ከክፈል 1 እሰከ 8