ሔፓታይትስ ኤ ቫይረስ

Hepatitis A Virus


ይህ ቫይረስ ጉበትን በቀጥታ ከሚያጠቁ ቁጥራቸው በርከት ካሉ ቫይረሶች አንዱ ነው። በዚህ ቫይረስ መለከፍ ጊዜያዊ የጉበት ቁስል በማስከትል በቀላሉ የሚያገግም ቀለል ያለ የበሽታ ስሜት ያስከትላል። በመሆኑም ምንም አይነት ለየት ያለ ሕክምና አይስፈልገውም። በሀገር ቤት ይህ በሽታ የወፍ በሽታ ተብሎ ይታወቃል። አንዳንድ ጊዜ ባልተለመደ ሁኔታ በሽታው ከበድ ያለ የህመም ስሜት በመፍጠር የጉበት መድከም በማስከትል ለሕይወት ማለፍ የሚያበቃ ደረጃ ይደርሳል። በዚህ በሽታ ተለክፈው ያገገሙ ሰዎች በደም ምርመራ ወቅት ለቫይረሱ ተጋልጠው የነበሩ መሆናቸውን የሚጠቁም ምልክት ያሳያል።

መተላለፊያ መንገዶች


ቫይረሱ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች አይነምድር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ዋነኛ መተላለፊያው መንገድ ከሰው ወደ ሰው በቫይረሱ የተነካካ ምግብና መጠጥ አማካኝነት ነው። ስለዚህ ይህ በሽታ ምጣኔ ሀብታቸው ባልበለፀጉ ሀገሮች በከፍተኛ ደረጃ ይገኛል ምክንያቱም በቂ የሆነ የመፀዳጃ አገልግሎት ባለመኖሩ በበሽታው የተለከፉ ሰዎች ዐይነምድር አማካኝነት ቫይረሱ የመጠጥ ውሃና ምግብ ወይም ለመጠጥና ለምግብ አገልግሎት የሚሆኑ ቁሳቁሶች በመነካካት ከሰው ወደ ሰው  ለመተላለፍ ስለሚያስችለው ነው።

የበሽታው ምልክትና ስሜቶች

ድካም ስሜት

ትኩሳት

ማቅለሽለሽ ማስታወክ እና ማስቀመጥ

ጠቆር ያለ የኮካኮላ መልክ ያለው ሽንት መሽናት

የጉበት ሕመም ስሜት (ሆድ ላይ በቀኝ በኩል ከጎን አጥንት ሥር ባለው አካባቢ)

ዐይን ላይ ቢጫ ምልክት መታየት የመሳስሉት ናቸው።


ምርመራ

ሐኪምዎ የሰውነት ምርመራና ቃለ ጥያቄ ተጨማሪ ሔፓታይትስ ኤ እና የጉበትን ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችል የደም ምርመራ ሊያዙልዎት ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ለሌሎች የጉበት ቫይረሶች ሔፓታይትስ ቢ እና ሔፓታይትስ ሲ Hepatits B and Hepatitis C የደም ምርመራ ያዙልዎት ይሆናል። በሕመም ምልክት ደረጃ ሶስቱም ቫይረሶች ተመሳሳይ ስሜት ሊይሳዩ ይችላሉ። ስለ ሔፓታይትስ ሲ እና ቢ በሌላ ክፍል እናቀርባለን።

 
መከላከያ

  • ለህፃናት ከአንድ አመት ዕድሜ በመጀመር ሁለት ክትባቶች በስድስት ወር ልዩነት ይሰጣል


  •   ለማንኛውም በሽታው በከፍተኛ ደረጃ በሚገኝባቸው ሀገሮች መኖር ወይም ለጉብኝት ለሚሄዱ


  •      ህገወጥ ዕፅ ለሚጠቀሙ ሰዎች


  •      የተመሳሳይ ዖታ የግብረ ስጋ ግኑኝነት ለሚፈዕሙ ሰዎች


ክትባቱ በሽታውን ለመከላከል ቢያንስ የሁለት ሳምንት ጊዜ ይወስድበታል። ስለዚህ መንገድ ከመጅመርዎ ከሁለት ሳምንት በፊት ክትባቱን መጀመር ያስፈልጋል።

ይህ በሽታ ዘላቂ የመሆን ወይም ስር የመስደድ ባህሪ የለውም።

በድንገት ለበሽታው የተጋለጡ ከመሰለዎት ወደ ሆስፒታል ጊዜ ሳይሰጡ በመሄድ ቫይረሱ ላይ የሚያተኩር ለየት ያለ መድሃኒት ማግኘት በሽታው አንዳይከሰት ይረዳዎታል።