በምሥሉ የሚታየው የኢቦላ ቫይረስ ነው፡፡

ጥሬ ዜና አለ፡፡ በኢቦላ ወረረሽኝ በክፉ ሁኔታ ከተጎዱ አገሮች ጊኒ የምትባል ነች፡፡ የሀገሬው ሰዎች በፈረንሳይኛ፣ ሲተረጎም “ኢቦላ ይብቃ” የሚል መፈክር ይዘው ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የክትባት ጥናት አካሄደዋል፡፡ ውጤቱም መቶ ፐርስንት መከላከል የሚችል መሆኑ ታውቋል፡፡ ከአሁን በኋላ ሞኝ የለም የሚሉ ይመስላል፡፡ ዘገባዎች እንደሚያስረዱት የበሽታው ሥርጭት መጠን ከሚታወቀው በላይ ነበር፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የበሽታው ምልክት ሳይኖራቸው ነገር ግን በቫይረሱ ተለክፈው እንደነበር በደም ምርምራ መረጋገጥ የታቸለ ብዙ ሰዎች መገኘታቸው ነው፡፡ የሞቱትን ነብስ ይማር እያልን፤ ሳይንስ ያበረከተውን ውጤት ማመስገን ነው፡፡ ከጀርባው ግን ገንዘብና የተለያዩ ሀገሮችና ተቋሞች ርብርብ መኖሩን ማውቅ ተገቢ ነው፡፡የአሜሪካው የብሔራዊ የጤና ኢንሰቲቲዩት (National Institute of Health –NIH) ደግሞ የክትባቱን ጥናት በማስፋፋት ሰዎች ላይ ሙከራ ሊያደርግ መሆኑ ተገልፆአል፡፡